ሥነ ምግባር
ሥነ ምግባር ማለት የሰዎችን ተግባር በመጥፎነትና በጥሩነት መክፈል እንደሚቻልና፣ ይህ ክፍፍል ሥርዓታዊ በሆነ መንገድ እንዲካሄድ ጥናት የሚያደርግ የፍልስፍና ክፍል ነው። የትኞቹ የሰው ልጅ ተግባራት እኩይ ሊባሉ ይችላሉ? የትኞቹስ ሰናይ ሊባሉ ይችላሉ? ሥርቆት እኩይ ከተባለ፣ መግደል እንዲሁ እኩይ ከተባለ፣ አንድ ሰው እህል ሰርቆ የተራበን ሰው እንዳይሞት ቢከላከል፣ ይህ ድርጊት እኩይ ነው ወይንስ ሰናይ? የቱ መሆኑን መለየት ካልተቻለ፣ በርግጥ አንድ ወጥ የሥነ ምግባር ሥርዓት መገንባት ይቻላልን? ወይንስ ማናቸውም የሥነ ምግባር ፍልስፍና በዘፈቀደ የተመረጠ ነው? እነዚህንና መሰል የሰው ልጅ ስለ ምግባሩ የሚሰጠውን ዋጋ የሚያጠና ክፍል ሥነ ምግባር ይባላል።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |