ቀበቶ (ማሽን)
(ከቀበቶ(ማሽን) የተዛወረ)
ቀበቶ ከተጣጣፊ ቁስ የተሰራ አንድ ዙር የሚሰራ፣ ሁለት የሚሽከረከሩ መዘውሮችን የሚያገናኝ የማሽን ዓይነት ነው። ቀበቶወች ለእንቅስቃሴ ምንጭ ሆነው ሊያገለግሉ ይችላሉ፣ ወይም ድግሞ ኃይል ለማስተላለፍ ወይም አንጻራዊ እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር ይረዳሉ። በቀበቶ ሁለትበከራወች በአንድ አቅጣጫ እንዲሽከረከሩ ማድረግ ይቻላል ወይም ከተፈለገ ቀበቶውን በማቋረጥ በተቃራኒ አቅጣጫ እንዲሽከረከሩ ማድረግ ይቻላል። በታላቅ የገበያ ቦታወች ላይ የሚሰራበት አመላላሽ ቀበቶ የዚህ ማሽን አንዱ ተግባራዊ መገለጫ ነው።