ሻማ ደረቅ ነዳጅ (ሰም) እና በውስጡ የተሸፈነ ቀጭን ገመድ (ክር) ያለው የብርሃን እና የሙቀት አመንጪ ነው። በአሁኑ ጊዜ አብዛሃኛዎቹ የሻማ ዓይነቶች የሚሠሩት ከፓራፊን ሲሆን በተጨማሪም ከንብ ሰም የሚሰሩም አሉ።

የተለኮሰ ሻማ ምስል

ሞራ የተሠሩ ሻማዎች በሮሜ ከ500 ዓክልበ.፣ በቻይናም ከ200 ዓክልበ. ጀምሮ ይታወቁ ነበር።