ስዌኖ
ስዌኖ በስዊድን አፈ ታሪክ ዘንድ ከያፌት ልጅ ማጎግ ቀጥሎ የስዊድን ንጉሥ ነበረ። ይህም በዮሐንስ ማግኑስ ተጽፈው በ1546 ዓ.ም. በታተመው ታሪክ መጽሐፍ ይገኛል። የማጎግ በኩር ልጅ ሲሆን የስዊድ ሕዝብ ከስሙ እንደ ተሰየሙ ተብሏል።
ማግኑስ የኡፕሳላ ኤጲስ ቆጶስ እየሆኑ፣ የስዊድን ጥንት ታሪክ በሩን ጽሕፈት መዝገቦች ተጽፎ እንዳገኙ አሉ። ይሁንና የዛሬ መምህሮች ትክክለኛ ታሪክ ሳይሆን እንደ አፈ ታሪክ ብቻ ይቆጥሩታል። ማግኑስ እንዳሉት ይህ ስዌኖ ለ115 ዓመት (ወይም ምናልባት 2427-2312 ዓክልበ. ግድም) ነገሠ፤ በዚያም ጊዜ ወንድሙ ጌጣር ደግሞ በጎረቤታቸው በጎጣውያን ወገን ይነግሥ ነበር። ከስዌኖ መሞት በኋላ ሌላ ወንድማቸው ኡቦ ተከተለው። አንዳንድ ሌላ ምንጭ ግን ስዌኖ ለ56 አመት ከነገሠ በኋላ ጌጣር በስዊድን ተከተለው የሚል ወሬ አለበት።[1]
- ^ Royal genealogies p. 424 - 1724 ዓ.ም. የታተመ (እንግሊዝኛ)