ብራቲስላቫ (Bratislava) የስሎቫኪያ ዋና ከተማ ነው። በታሪክ መዝገብ «ብረዛላውስፑርክ» (Brezalauspurc) ተጽፎ መጀመርያው የታወቀ በ899 ዓ.ም. ነበር። በ992 ዓ.ም. ገደማ በወጡ መሐለቆች ደግሞ ስሙ «ብራስላቫ» ወይም «ፕሬስላቫ» ተጽፎ ይገኛል። ይህም በጀርመንኛ Pressburg (ፕሬስቡርግ) ስለ ሆነ እስከ 1911 ዓ.ም. ስሙ ያው ሆነ። በ1911 ዓ.ም. ስሙም ወደ ብራቲስላቫ ተቀየረ።

የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር 426,091 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 48°9′ ሰሜን ኬክሮስ እና 17°6′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለ ብራቲስላቫ የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።