ሲን-ኤሪባም
ሲን-ኤሪባም ከ1753 እስከ 1751 ዓክልበ. ድረስ (ኡልትራ አጭር) የላርሳ ፮ኛ ንጉሥ ነበረ። የሲን-ኢዲናም ተከታይ ነበር። የአባቱ ስም አይታወቅም።
ለዘመኑ ፪ ዓመታት የዓመት ስሞች ታውቀዋል። እነርሱም፦
- 1753 ዓክልበ. ግ. - «ሲን-ኤሪባም ንጉሥ የሆነበት አመት»
- 1752 ዓክልበ. ግ. - «ታላቅ የመዳብ ሐውልት ወደ ቤተ መቅደስ ያመጣበት ዓመት»
- 1751 ዓክልበ. ግ. - «ሲን-ኢቂሻም ንጉሥ የሆነበት ዓመት»
ሲን-ኤሪባም በኒፑር ላይ የላርሳ ሥልጣን አስቀጠለ። የሲን-ኤሪባም ተከታይ ልጁ ሲን-ኢቂሻም ነበረ።
ቀዳሚው ሲን-ኢዲናም |
የላርሳ ንጉሥ 1753-1751 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ ሲን-ኢቂሻም |
የውጭ መያያዣ
ለማስተካከል- የሲን-ኤሪባም ዓመት ስሞች
- የላርሳ ንገሥታት Archived ኦክቶበር 21, 2012 at the Wayback Machine (እንግሊዝኛ)