ሯይጛ ብሔር
ሯይጛ ብሔር በምየንማ የሚኖር ብሔር ነው። አብዛኛዎቹ ዛሬ የእስልምና ተከታዮች ናቸው፤ ጥቂቶቹም የሂንዱ ሃይማኖት ምእመናን ናቸው። ትውልዳቸው ቋንቋቸውም እንደ ሕንዳዊ-ኢራናዊ ቋንቋዎች አባላት ወይም እውነተኛ «አርያኖች» ናቸው።
ከጥንት ጀምሮ በዚያ አካባቢ ቢገኙም፣ ከምየንማ ቡዲስም መንግሥት ወይም ሕዝብ ዘንድ አሁን የዜግነት ተቀባይነት ስላላገኙ ሯይጛዎቹ በዜና ላይ ታይተዋል። በምየንማም መንግሥት አስተያየት ዘንድ፣ ሯይጋ በባንግላዴሽ መኖራቸው ይሻላቸው ነበር።
የብሐሮች ሃይማኖቶች፣ ቋንቋዎች፣ ታሪኮችና ስንኳ የስያሜዎች አጠራሮች ወዘተ. በዚህ የአለም ክፍል ከጥንት እጅግ ውስብስብ ናቸው። ደግሞ ዳኛዋቲን ይዩ።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |