ራያ

ማለት በስሜን ወሎ እና በደቡብ ትግራይ ሰፍሮ የሚገኝ ህዝብ ነው

፭ራያ ማለት በሰሜን ወሎ እና በደቡብ ትግራይ የሚገኝ ህዝብ ነው። ይህ ህዝብ የራሱ የሆነ ባህል እና ወግ፡ ማለትም እንደ አነጋገር፡ አለባበስ፡ የሰርግ ፡ የለቅሶ ስነስርዐት ያለው ኩሩ እና ጀግና ህዝብ ነው። የራያ ህዝብ ከሚደነቅበትና ከሚያስደስት ባህሉ ሁሉም የእምነት ተከታዮች በተለይምሙስሊም ክርስቲያንሳይል በመቻቻል በህብረት በአንድ ላይ ተከባበሮ የሚኖር ህዝብ ሲሆን የአለባበስ ባህሉ ሌላው የሚደነቅለት አና ባህላዊ ጭፈራው ሲያዩት የሚያስግርም አና የሚያስድስት ነው። ከባህላዊ ጭፈራዎቹ እንደ "ጉማየ" "መጋልዋ" ፡ ወዘተ መጥቀስ ይቻላል፡፡ ህዝቡ የሚኖርበት አከባቢ እንደሚከተለው ይዋሰናል። በሰሜን እንደርታ፡ በደቡብ የጁ፡ በምስራቅ አፋር እንድሁም በምእራብ ላስታ ያዋሱኑታል። የከተሞች ስም ለመጥቀስ ያክል አላማጣቆቦኮረምማይጨውመሆኒ ጨርጨር በመባል ይታወቃሉ። የህዝቡ አስተዳድር እንደየ መንግስቶቹ ስቀያየር የኖረ ሲሆን፡ ቀደም ስል ራያን በሁለት አውራጃዎች በመክፈል ራያ ና ቆቦ ማእከሉ አላማጣራያ ና አዘቦ ማእከሉ ማይጨው በማድረግ በወሎ ጠቅላይ ግዛት ስር ይተዳድር ነበር።ራያ ቆቦ በአሁኑ ሠአት ወረዳ ሢሆን ማዕከሉ ቆቦ ነው በሥሩ ብዙ ቀበሌዎች አሉት ለምሣሌ 07 አቧሬ አንዷናት። ምንጭ ከራያ ኣባቶች