ዩክሊድ ወይንም የእስክንድርያው ዩክሊድ ( 325 ዓ.ዓ.–265 ዓ.ዓ.) የጥንቱ ዘመን ገናና የሒሳብ ተማሪ ነበር። ዩክሊድ እስክንድርያግብፅ አገር በእስክንድርያ ቤተ መጻሕፍት ተቀጥሮ ይሰራ ነበር። ከዘመኑ ርዝመትና ከመዝገብ መጥፋት አንጻር፣ የዩክሊድ ህይወት ታሪክ እምብዛም አይታወቅም።

የዩክሊድ ሃውልት፣ በኦክስፎርድእንግሊዝ

ኢለመንትስ (ታዋቂው የዩክሊድ መጽሐፍ)

ለማስተካከል

ዩክሊድ፣ የነበረበትን ዘመን የጂዎሜትሪ ዕውቀት በማሰባሰብ ኤሌመንትስ የተሰኘውን መጽሐፍ ለመድረስ ቻለ። ይህ መጽሐፍ ከጥንት ጀምሮ እስከ አሁን ዘመን ድረስ ለጅዎሜትሪ ትምህርት መሰረት ሆኖ ያገለግላል።

የዩክሊድ መጽሐፍ ከአንስተኛ ቁጥር ያላቸው የጂዎሜትሪ እሙኖች በመነሳት አምክንዮን በመጠቀም ወደ ብዙ እርግጦች በመሻገር የጂዎሜትሪና የቁጥር ጠባያትን ከጥርጥር ውጭ በሆነ መልኩ ይገልጻል።

የኤለመንትስ መጽሐፉ፣ በተጨማሪ፣ ስለእይታ (ፔሬስፔክቲቭ)፣ የሾጣጣ ክፍሎችሉላዊ ጂዎሜትሪ እና ኳድራቲክ ገጽታዎች ያትታል። ከጂዎሜትሪ ጎን ለጎን የቁጥር ኅልዮትም በሚገባ መልኩ በዚሁ መጽሐፍ ተመርምሯል። ታላቁ የጋራ አካፋይ የተሰኘውን የሥነ ቁጥር መሳሪያ በዚሁ መጽሐፍ በዩክሊድ ተደርሶ ይገኛል።

ዩክሊድ ያስቀመጠው የጂዎሜትሪ ስርዓት ለብዙ ዘመናት ጅዎሜትሪ በመባል ሲታወቅ፣ እስከ 19ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ እንደ ብቸኛ ጂዎሜትሪ ይወሰድ ነበር። ሆኖም ግን በዚሁ ዘመን በተነሱ ሌሎች አይነቶች ጂዎሜትሪዎች፣ የርሱ ስርዓት ዩክሊዳዊ ጅዎሜትሪ በመባል ይታወቃል። ይሄውም ከኢ-ዩክሊዳዊ ጅዎሜትሪ ልዩ መሆኑን ለማሳየት ነው።

ከኤሌመንትስ በተጨማሪይ የዩክሊድ ሌሎች 5ስራዎች እስከ አሁን ዘመን ድረስ ዘልቀው ይገኛሉ። እኒህ 5 ስራዎች በይዘታቸው ከኤልመንትስ ጋር ተመሳሳይ ናቸው።

 
እጅግ ጥንታዊ የሆነ የዩክሊድ ኤሌመንትስ መጽሐፍ ቅሪት (100 ዓ.ም.) ። ምስሉ ከኤሌመንትስ መጽሐፍ 2፣ እርግጥ 5 ይመነጫል [1]


  1. ^ Bill Casselman. "One of the oldest extant diagrams from Euclid". University of British Columbia. በ2008-09-26 የተወሰደ.