ማርጯ
ማርጯ በዘማነ መንግሥታት የወላይታ ህዝብ ይጠቀምበት የነበረው የመገበያያ ገንዘብ ነው። ይህ ገንዘብ ከብረት የተሰራ እንደሆነ ጸሐፍት ያረጋግጣሉ። ገንዘቡ የ፲፰ ኢንች ያህል ርዝመት አለው። ዋጋውም ፲፰ ማሪያ ትሬዛ ወይም 0.50 የአሜርካ ዶላር ጋር እኩል ነው።[1][2]
ታሪክ
ለማስተካከልስቲገድ(፲፰፻፸፯ - ፲፱፻፲፱) እንደጻፈው ከሆነ ወላይታ ጥጥ እና የጥጥ ውጤቶችን በመጠቀም በኢትዮጵያ ቀዳሚ መንግሥት ነው። ለወላይታ ግን እነዚህ የጥጥ ውጤቶች ከልብስነት ያለፈ ጥቅም ነበረው። እንደምሳሌ ሻሏ እና ካሬታ ሲና ቢወሰድ፣ በወላይታ የመንግሥታት ታሪክ እንደየአቀማመጣቸው ለበርካታ ምዕተ ዓመታት እንደ ገንዘብ አገልግሎት ላይ ውለዋል። [3]
ከካሬታ ሲና ቀጥሎ ወላይታ ወደ ከፍተኛ የተክኖሎጂ እደገት ላይ ደረሱ፤ ከዛም ብረት አቂልጦ የተሻሻለና ዘመናዊ ገንዘባቸውን ጥቅም ላይ አዋሉ። ይህኛው ገንዘብ ስሙ ማርጯ ይባላል። ወላይታ ህዝብ በዳግማዊ ዐፄ ሚኒልክ እና አባ ጅፋር ጦር ከተደረገ እልህ አሰጨራሽ ጦርነት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ መንግሥት እስከተቀላቀበት ደረስ ማርጯን እንደ ገንዘብ ይጠቀምበት ነበር። ምንጮች እንደምጠቁሙት ከሆነ በዳግማዊ ዐፄ ሚኒልክ ግፊት ኢትዮጵያን ከመቀላቀላቸው በፊት ሐድያ፣ ሲዳማ፣ ዳውሮ፣ ጋሞ፣ ጎፋ እና ከምባታ የወላይታን ማርጯ እንደመገበያያ ይጠቅሙበት ነበር።[4]
ወላይታ የራሱን ገንዘብ በመጠቀም በምሥራቅ አፍሪቃ ብቸኛ ጎሳ ነው። ማርጯ ተክለ ሐይማኖት በወላይታ ይሰብክ በነበረበት እስከ ካዎ ሞቶሎሚ ዘመነ መንግሥት ጊዜም ማለትም እስከ ፲፪፻፸ ድረስ እንደነበር ጸሐፍት ያረጋግጣሉ።[2]
ዋቢ
ለማስተካከል- ^ Argaw Yimam, Ass. Professor Wondu. "Power Consolidation, Modernization and Commercial Splendor in Pre-Colonial Africa: The Case of Wolaita Kingdom (1500's 1894)".
- ^ ሀ ለ Vanderheym, J.-Gaston Auteur du texte (1896) (in EN). Une expédition avec le négous Ménélik : vingt mois en Abyssinie... / J.-G. Vanderheym ; [préface de Jules Claretie]. https://gallica.bnf.fr/ark:/12148/bpt6k62093097.
- ^ Stigand, C. H. (Chauncey Hugh). (1910). To Abyssinia through an unknown land: an account of a journey through unexplored regions of British East Africa by Lake Rudolf to the kingdom of Menelek.
- ^ Argaw Yimam, Ass. Professor Wondu. "Power Consolidation, Modernization and Commercial Splendor in Pre-Colonial Africa: The Case of Wolaita Kingdom (1500's 1894)".