የጌዞ ብሔረሰብ ቋንቋ ‹ጌዞኛ› ሲሆን፣ ቋንቋው ከማዕከላዊ ኦማዊ ቋንቋዎች ቤተሰብ ይመደባል።

ሕዝብ ቁጥር

ለማስተካከል

በ1999 ዓ.ም በተደረገው የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ውጤት የብሔረሰቡ ሕዝብ ብዛት 363ሺ9 ነው፡፡

መልክዓ ምድር

ለማስተካከል

ጎፋዋናከተማ

የዑባ ካቲ (ንጉሥ) ግዛት

   የዑባ አካባቢ ነፃ የተደራጀ ባህላዊ የፖለቲካ አስተዳደር የተፈጠረው ከአሪ ግዛት ተነጥሎ ዑባ ነፃ አስተዳደር ግዛት ከሆነበት ዘመን ወዲህ ነበር ።  የዑባ ጥንታዊ ግዛት በሰሜን ዜንቲ ወንዝ : በደቡብ ምስራቅ የማዜ ወንዝ ይዞ እስከ ዛላና ዑባ መካከል ያለው ሸለቆ አልፎ ዘቃ ዛልቶ እና ጋላዳ ቀበለያትን ያካትታል ። በደቡብ ማሌ ወረዳ : በደቡብ ምዕራብ የአሪ ግዛት: በምዕራብ ሙሉ በሙሉ በአሪ ግዛት ይዋስናል ።የካቲው (የንጉሱ) አስተዳደር ሥርዓት ለብቻ የተዘረጋው ከአሪ ማዕከል የመጣው ንጉስ ሾዴ (shodh) ከነገሰበት ጊዜ ጀምሮ ሲሆን ይህንን ከላይ የተጠቀሰውን አካባቢ ይገዛ የነበረው የዚህ ትውልድ ነበር ።

     መጀመሪያ ከአሪ ወደ ዑባ አካባቢ የመጣው ሰው የተቀመጠው በዑባ ተራራማ አካባቢ አምፖ በሚል ስም በሚታወቅበት ቦታ ነበር ከዚህ በመነሳት የጎሳው ዝሪያዎች ቀስ በቀስ ግዛት አስፋፍተው ሊቆጣጠሩ እንደቻሉ ይገለፃል ። በአካባቢው የካቲ አስተዳደር  ከተመሠረተ በኋላ ሰሜናዊ የግዛት ክፍል ማለትም መላና አካባቢውን : ጋልጣና አካባቢውን በመልቀቅ ወደ ደቡብ ምሥራቅ በማስፋፋት ጥንት የባዮ ግዛት የነበረውን ዙዛና አካባቢውን : ጋላዳና አካባቢውን ያዘ ። በሰሜናዊ ግዛት የጎፋ እና የዛላ ካቲ አይለው በነበሩ ጊዜ ዑባን በኃይል አስለቅቀው ወደ ደቡብ እንድዞር አደረገዋል ይባላል ። የጎፋ እና የዛላ ካቲታይ(ንጉሶች) ፍላጎት ከፍ እያለ በመጣበት ወቅት የዑባ ካቲ ላይ በጦርነት እነዚህን ቀበሌያትንና አካባቢውን በኃይል አስለቅቀው እንደያዘ ይነገራል ።

    ወደ ዑባ ተሻግረው ከነገሰው ሾደ(shodhe) ነጥቀው በትውልድ ሀረግ ቆጠራ መሠረት የሚቀጥሉ ካቲዎች በዑባ ነግሰዋል::

1. ጋልታይዛ                  8. አይሳ

2. ሾጴ ( shodhe)         9. ታንጋ

3. ፖሻ                        10. ሉፀ

4. ቱጫ                       11. ኦፈ

5. ቶልባ                      12. ኩንሳ

6. ቦላ                         13. ዲቻ   ናቸው

7. ካንሳ ነበሩ ።

እነዚህ ነገስታት ዑባን ከዳር እስከ ዳር ያስተዳደሩ የነበሩት አከባቢው ወደ ማዕከላዊ መንግስት አስተደደር ሥር እስከሚሆን ድረስ ነበር ።

      ዑባን ከገዙት ካቲዎች ውስጥ ድንበር ከማስከበር አልፎ ጦርነቶችን አካሄዶ የተወሰኑ ግዛት ክፍሎችን በኃይል እንደያዘ የሚነገረው ካቲ ቦላ ነበር ። ካቲ ቦላ በጣም ጦረኛ ስለነበረ ህዝብን አሰልፎ ከጎፋ እና ከዛላ ጋር በሚዋስኑ አካባቢዎች ድንበሮችን ለማካለል የበቃ ካቲ ነበር ። ከአሪ ግዛት ጋር ያለውን ውስጣዊ የዝምድና ትስስር በመበጠስ ወደ ጦርነት ገብቶ ድንበሩ እንድካለል ያደረገው እሱ እንደነበረ ይነገራል ።

       የዑባ ካቲ አስተዳደር ሥርዓት የጀመረው ከዑባ ዣላ ከፍ ብሎ በሚገኘው አምፖ በሚባለው ቦታ ነው ። እዚሁ መጀመሪያ መጥቶ የነገሰው ካቲው ሾዴ ( shodhe) ሲሆን ሶስት የአምልኮ : የአስተዳደር ማዕከል  እና የመኖሪያ ቦታዎችን በማበጀት ማስተዳደር  ጀመረ ። በዚሁ መሠረት ዶጃ የነጋሲያን የአምልኮ ሥፍራ እና አምፖ የአስተዳደር ማዕከል ካምባ የመኖሪያ ቦታ አድርጎ በዚሁ ተራራ ላይ አዘጋጀ ። ከዚያን በኋላ ጥንታዊ የዑባ ግዛት ተብሎ የሚታወቀውን አካባቢ ይገዙ የነበሩ ካቲዎች ዋና መኖሪያቸውና የአስተዳደር ማዕከላቸውን እዚሁ አድርገዋል። ሆኖም ከኋላ አስተዳዳሩ እየተጠናከረ ሲሄድ ዣላ : ቡኔ : ጋልፃ እና በሌሎች ቦታዎች መቀመጫቻውን ያደረጉት የበታች ተሿሚዎችን ተጠርነቱን ለካቲው ሆኖ ሲያስተዳድሩ ቆይቷል ። ከላይ በተጠቀሱት የአስተዳደር አካበቢዎች  ኃላፊነት ይዘው ያስተዳደሩት የነበሩ '' ማይጫ ዳና '' የሚል ማዕረግ ስም የያዙት ነበሩ ።

        በዚህ አቅጣጫ ካቲዎች ህዝብንና መሬትን በበላይነት ይመሩ እንደነበሩ የዕድሜ ባለፀጎች መረጃዎች ያስረዳሉ ። ሌላው ደግሞ ማይጫ ዳና ሥር የአስተዳደር ሥራዎችን ከመሥራት አኳያ ትልቅ አስተዋፆኦ እንደነበራቸው የሚነገርላቸው የሚባሉ ሳጋ እንደ ቃልቻ ያሉ ረግመውና መርቀው የሚያደርሱ ይገኙ ነበር ። ሥራቸውንም ሊያከናወኑ ህዝብ የከበረታ ሥፍራ ይሰጣቸው ነበር ። ሌሎች ደግሞ በህዝብ ውስጥ የሚሠሩ ባህላዊ አምልኮ አስፈፃሚዎች ብታንቴ የሚባሉት በየቀበሌያት ይገኙ ነበር ።

        በነፃ ግዛት ይኖር የነበረው ህዝብ በአዋሳኝ ከሚገኘው ህዝብ ጋር ተቀላቅሎ በጎሳ ሥርጭት : በባህል አንድ ሆኖ ኖረዋል ። ይሁንና የካቲ አስተዳደር እየተጠናከረ በሄደበት ወቅት ከጎፋም : ከዛላና ከሌሎች ደቡባዊ አቅጣጫ ከሚገኙት ጋር ጦርነቶችን አካሂደዋል ። ከዛላ ካቲ ግዛት ጋር መሀላ ፈጽመው የውል ስምምነቱን ጨርሰው የኖሩት ዑባ ዙማ ተብሎ በሚጠራ ቦታ በተደረገው እርቅና ስምምነት ነበር ።  በጎ ፋ ካቲ ካንሳና በዑባ ካቲ አይሳ መካከል ከፍተኛ ጦርነት በተካሄደበት ጊዜ በዑባ ጋይላ ላይ በተደረገው ውጊያ የመራውን ካቲ ካንሳን ወግቶ ካቆሰለ በኋላ እንደሞተ ይነገራል፡፡

       በዚያን ዘመን በነዚህ አካባቢዎች ጦርነቶች ሲከፈቱ አንዱ ከሌላው ወገን ጋር ለማስታረቅ ጥረት የሚያደርጉት ራሳቸው ካቲዎች ነበሩ፡፡ ይህንን ሚና ካቲዎች የሚጫወቱት የሠላም ምልክት አድርገው በሚወስዱት የመልዕክት ልውውጥ ነበር፡፡ ይኽውም ቀድሞ ሰላም ፈላጊ ካቲው የራሱን መርኩዝ ለሌላኛው ካቲ በመላክና የዚያኛውንምርኩዝ የላከው መልዕክተኛ ይዞ ሲመጣ ነበር፡፡ ይህንን መጀመሪያ በመስጠትና ምላሽ የማግኘት ሥርዓት kollo hellisse በመባል የሚታወቅ ሲሆን በዚህ ሁኔታ ሁለቱም ወገኖች ወደ እርቅ ድርድር ይገቡ ነበር፡፡

      ካቲዎች ትልቅ አክብሮት ከህዝብ የሚሰጣቸው ሲሆን ሥልጣናቸውም ከመለኮታው ኃይል እንደሆነ አድርገው ይወስዱ ነበር፡፡ ስለዝህም ካቲው በዑባ በጣም ይከበራል፤ ህዝቡም ይታዘዝለት ነበር፡፡ የአነጋገስ ሥነ-ሥርዓትም በተመለከተ ለአጎራባች ካቲዎች እንደሚደረግላቸው ዓይነት ነው፡፡ ይኸውም ለካቲዎች የሚደረግ ክብር መለክያ ዕቃዎች ተመሳሳይነት እና ካቲው ሲሞት የሚተካው የካቲው ታላቅ ልጅ መሆኑ ነው፡፡ ነገር ግን ሳጋ የሚባሉት ከሌሎች አንጋሾች ጋር በመሆን ካቲው በሚነግስበት ወቀት ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱት ክፍል እንደሆነ ይነገራል፡፡በዑባ የካቲ አስተዳደር መጀመር ተከትሎ በአጎራባች ከሚገኙት ካቲ ግዛቶች ጋር ያለው ግንኙት መልክ እየያዘ መጥቷል፡፡ቀደም ሲል በአከባቢው እንደነበሩ የሚነገሩ ጎሳው ተቋዋሚዎች ፈርሰው የአሪ ግዛት እየተጠናከረ እንደመጣ ብዛት ያላቸው ማህበረሰቦች በየቦታው በአይካ መንግሰት ሥር ሆነው ሲተዳደሩ ቆይቷል ፡፡   ብሔረሰብ በጋሞጎፋ ዞን ውስጥ ከሚገኙ ብሔረሰቦች መካከል አንዱ ሲሆን፣ ብሔረሰቡ በዋናነነት በጎፋ ዙሪያ፣ ዛላ፣ ዑባ፣ ደብረፀሐይ እና መሎካዛ በሚባሉ ወረዳዎች ይገኛል፡፡ የብሔረሰቡ ዋና የሀብት መሠረት ጥምር ግብርና ሲሆን፤ የገቢ ምንጭ በሚያስገኙ ምርቶች ላይ የተመሠረተ ነው፡፡

የጎፋ ብሔረሰብ የራሱ የሆነ ነባር ባህላዊ አስተዳደር አለው፡፡ ጥንት በጎፋ ግዛት ክልል ሥር የነበሩ አካባቢዎች በሰባት የካዎ (ነጉሥ) ግዛቶች ተከፋፍለው የተደራደሩ ነበሩ፡፡ እያንዳንዱ ከአዎ የአስተዳደር ማዕከል ቤተ-መንግሥት(ጋዶ) ነበረው፡፡ ማዕከላዊ አስተዳደሩ የተለየ ሥልጣንና የሥራ ድርሻ ያላቸውን አስፈፃሚ አካላትን የያዘ ነበር፡፡ ካዎ (ንጉሥ)- የባህላዊ አስተዳደሩ ቁንጮና ከፍተኛ የሥልጣን አካል ሲሆን፤ ከእርሱ ቀጥሎ የሚገኙትን የሥልጣን አካላትንና አማካሪዎችን የመሾምና የመሻር ሥልጣን ነበረው። ጠንከር ያለ ውሳኔን የሚሹ ጉዳዮች የመጨረሻ ብይን የሚያገኙትም በካዎ ነበር፡፡

ብሔረሰቡ ጋብቻ የሚፈጸመው የጎሣ አቻነትን፣ የሀብት ደረጃ በማስተያየትና የሥጋ ዝምድና አለመኖርን መሠረት በማድረግ ነው፡፡ ወንዶች ከ17-25፤ ሴቶች ደግሞ ከ14-19 ባለው የዕድሜ ክልል ጋብቻ ይፈጽማሉ፡፡ ሴቶችም ሆኑ ወንዶች ጋብቻ ከመፈጸማቸው በፊት ይገረዛሉ፡፡ ጋብቻ ከመፈጸማቸው በፊት ሴቷ ጥጥ ፈትላ አልባሳት ስታዘጋጅ ወንድም በፊናው የመኖሪያ ቤትና የራሱን የእርሻ ቦታ ያደራጃል፡፡

በብሔረሰቡ የተለያዩ የጋብቻ አፈጻጸም ሥርዓቶች አሉት፡፡ በቤተሰብ ስምምነት፣ በጠለፋ የሚፈጸሙ ጋብቻዎች ኣሉት። በተጋቢዎችም ሆነ በቤተሰብ መካከል ያለመግባባት ሲከሰት ወይም የአግቢው ገቢ ሀብት አቅም ውሱንነት ሲከሰት ተጋቢዎቹ ሳይተዋወቁ የወንዱ አባት ሽማግሌ ይዞ የልጅቷን ቤተሰብ ከ1-2 ቀን ደጅ በመጥናት የሚፈጸም የሽምግልና ጋብቻም ኣለው። የምትክ ጋብቻ የሚባለው ደግሞ፤ ሚስት ከሞተች እህቷ ወይም የቅርብ ዘመዷ በምትክ ሚስትነት የምትሰጥበት የጋብቻ ኣይነት ነው፡፡ ወዶ ገብ ጋብቻ ደሞ ሌላው በብሔረሰቡ የሚፈጸም የጋብቻ ዓይነት ነው፡፡ ይኸውም፤ ሳታገባ የቆየች ሴት የራሷን ንብረት በመያዝ ወደ ወንዱ ቤት በፈቃዷ ሄዳ በመግባት የሚፈጸም የጋብቻ ዓይነት ነው፡፡

በብሔረሰቡ በበዓላት ቀናት ከሚዘጋጁት ምግቦች መካከል ሸንዴራ ይገኝበታል፡፡ ከበቆሎና ከገብስ ዱቄት የሚሠራ ሆኖ ቅመማቅመምና ቅቤ በማጣፈጫነት ገብቶበት የሚበላ ጥሩ ምግባቸው ነው፡፡ ቡላ በአይብ ጎመንና ቅቤ ገብቶበት የማሠራው ‹‹ባጭራ›› የተባለው ምግባቸውና ‹‹ቅንጬ›› በበዓላት ቀን ከሚያዘጋጇቸው ተጠቃሾች ናቸው፡፡

ጐፋዎች በነባሩ ባህላቸው ከቆፋ፣ ከሌጦና ከጥጥ የተሠሩ አልባሳትን ይጠቀሙ ነበር፡፡ ‹‹ኢቴ›› የማባለው ከቆዳና ከሌጦ የሚሠራውን ልብስ ወጣቶችና አዋቂዎች በጀርባቸው ላይ ጣል በማድረግ ከወገባቸው ብቻ ‹‹አሣራ›› (ዲታ) የሚባለውን ከጥጥ የሚሠራ ግልድም ያገለድማሉ፡፡ ማንቾ (ማሽኮ) ዕድሜያቸው ከ1-8 የማሆናቸው ሴት ሕፃናት ደሞ ከድርና ማግ አልፎ አልፎም ከቆዳ ተገምዶ ጫፉ ላይ በዛጎል ያጌጠን ልብስ ለብልታቸው መሸፈኛ ይታጠቁታል፡፡ በባህላዊ ሽመና የሚሠሩ ቡልኮ፣ጋቢ፣ነጠላ፣መቀነት ወዘተ… በብሔረሰቡ በብዛት የሚዘወተሩ አልባሳት ናቸው፡፡

የብሔረሰቡ አባል ሲሞት ለባህላዊ መዎች፣ ለአዛውንቶች፣ ለጎልማሶችም ሆነ ለወጣቶች ‹‹ዘዬና›› ‹‹ዳርበ›› የሚባለውን የሙዚቃ መሣሪያ በመምታት የአካባቢው ማኅበረሰብ እንዲሰበሰብ ይደረጋል፡፡ የሞተው ንጉሡ ከሆነ ሁሉም ሰው ግንባሩን ጥላሸት ወይም ጭቃ በመቀባት በፀጉሩ ላይ ደግሞ አመድ በመነስነስ ‹‹ሰማይ ተናደ›› በማለት ያለቀሳል፡፡ የለቅሶው ርዝማኔ እንደሟች ክብርና ዝና ከ4-7 ቀናት ይቆያል፡፡

ታዋቂ ሰዎች

ለማስተካከል

ጎፋ የኢትዮጵያ ብሔር ነው።