ሙላቱ አስታጥቄ
ሙላቱ አስታጥቄ አንጋፋ ኢትዮጵያዊ ሙዚቀኛ ሲሆን ኢትዮ ጃዝ የተባለውን የሙዚቃ ስልት በመፍጠር የኢትዮጵያን የጃዝ ሙዚቃ ዕድገት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ያደረሰ ሰው ነው። ሙላቱ በዚህ ሥራው ከመወደዱና ከመደነቁም ሌላ በዓለም ላይ ብዙ የኢትዮ ጃዝ አፍቃሪዎችን አፍርቷል። በሥራውም የአብራውዝ ግራንት አሸናፊ ሆኗል።[1]
Life story
ለማስተካከልሙላቱ አስታጥቄ በጅማ ከተማ በ1935 ዓ/ም ተወለደ። የልጅነት ጊዜውን አዲስ አበባ ውስጥ ያሳለፈው ሙላቱ በትምህርቱ ጎበዝ ስለነበረ ቤተሰቦቹ ለትምህርት መሐንዲስነት (ኢንጅነሪንግ) አንዲያጠና ወደ ታላቋ ብሪታኒያ ቢላክም ውስጡ በነበረው የሙዚቃ ፍቅር ተልእኮው የሙዚቃ ሆነ። ብርቅዬው የሙዚቃ ቀማሪ ላለፉት 40 ዓመታት በ'ጃዝ' ሙዚቃ ውስጥ ኖሯል። ኢትዮጵያን ለዓለም በ'ጃዝ' ያስተዋወቀው ሙላቱ አለማኛ ውስጥ በስሙ መንገድ ተሰይሞለታል፣ በአሜሪካም የበርክሊ የሙዚቃ ኮሌጅ የመጀመሪያው ጥቁር የሙዚቃ ተማሪ ነበር። ሙላቱ በዚሁ ኮሌጅ የአፍሪቃን ትምህርቶች ክፍል አማካሪነት ሹመት አግኝቷል። ሙላቱ አስታጥቄ «ብሮክን ፍላወር» የተባለው ፊልም ላይ ሙዚቃ በመሥራት ትልቅ አድናቆትን አግኝቷል። ይህም ለኢትዮ ጃዝ ሙዚቃ ዕድገትና በዓለም ላይም ትልቅ ደረጃ እንዲያገኝ ረድቶታል።[1]
ሙላቱ ለዓለም አቀፋዊ የሙዚቃ እድገት ስላደረገው ታላቅና ጉልኅ አስተዋፅፆ፤ በተጨማሪም በቀድሞ ኮሌጁ ተማሪዎች ላይ ስላሳደረው አርአያነት በቦስቶን የሚገኘው የበርክሊ የሙዚቃ ኮሌጅ ግንቦት 4 ቀን 240ዓ/ም ሙላቱን የክብር ዶክቶሬት ዲግሪ ሸልሞታል።[1]
የፀሀፊው
ለማስተካከል- ^ ሀ ለ "ናሽናል ቢብሊዮግራፊ ቡድን፣ የአንጋፋ አርቲስቶች መዝገበ የሕይወት ታሪክ፣ መጋቢት ፳፻፣ ገጽ 32". Archived from the original on 2011-09-29. በ2010-12-18 የተወሰደ.