ሜኒስ (ሜኔስሜኒ) የግብጽ ቀድሞ ዘመን መንግሥት መጀመርያው ፈርዖን ይባላል። በግብፅ ታሪክ እንደ ተለመደው ላይኛ ግብፅታችኛ ግብፅ መጀመርያ በአንድ መንግሥት ያዋሀደው እሱ ነበረ።

የሜኒስ መታወቅያ ትንሽ ተከራካሪ ጉዳይ ሲሆን፣ በአብዛኛው የዛሬ ሊቃውንት አስተሳሰብ በኩል፣ ሜኒስ ለሥነ ቅርስ ከሚታወቀው ፈርዖን «ናርመር» ከተባለው ጋር አንድ ነው።

የግሪኩ ታሪክ ጸሐፊ ሄሮዶቶስ እንደሚለው፣ በሜኒስ ዘመነ መንግሥት መጀመርያ፣ ስሜን ግብጽ በሙሉ አሮንቃ ነበረ። ሜኒስ ግን ሰዎች በዚያ እንዲኖሩ ጨቀጨቁን አደረቀውና ሜምፊስን (ግብጽኛ፡ «ኢነብ ኸጅ» ወይም ነጭ ግድግዳ) ሠራ።

ሌላ ግሪክ ጸሐፊ ዲዮዶሮስ ሲኩሉስ በተጨማሪ ሜኒስ መጀመርያው ሕግ-ሰጪ እና ሃይማኖት-ሰጪ እንደ ነበር፣ ከዚህም በላይ በግቢው ውስጥ ምቹና ውድ ኑሮ እንዳስገባ ብሎ ጻፈ። ስለዚሁ መረንንነት የኋለኛ ዘመን (22ኛ ሥርወ መንግሥት) ፈርዖን ትኔፍራክቶስ ሜኒስን እንደ ረገመው ዲዮዶሮስ ይለናል። በዲዮዶሮስ ታሪክ፣ ሜኒስ በሞኤሪስ ሐይቅ ላይ በውሾቹ ተዋጋ፣ በአዞ እርዳታ ግን አመለጠ፤ ከዚያም «አዞ ከተማ» (ክሮኮዲሎፖሊስ ወይም ሸድየት) የሚባል ከተማ ሠራ።

ሌላ ታሪክ ጸሐፊ ፕሊኒ እንደ ጻፈ ደግሞ፣ ሜኒስ መጀመርያ ጽሕፈትን የፈጠረው ነበረ።

በግብጻዊ ታሪክ ጸሐፊ በማኔጦን መሠረት፣ ሜኒስ የጢኒስ ኗሪ ነበረ፤ 62 ዓመት ከነገሠም በኋላ በጉማሬ ተገደለ። ማኔጦን የሜኒስን ተከታይ አጦጢስ ይለዋል፤ በሌሎች ጥንታዊ የግብጽ ነገሥታት ዝርዝሮች መሠረት የ2ኛው ፈርዖንና የሜኒ ተከታይ ስም ቴቲ (ወይም ኢቴቲ) ተባለ። ከሥነ ቅርስ የታወቀው «አሃ» ወይም «ሆር-አሃ» የተባለው ሁለተኛው ፈርዖን እና ይህ ቴቲ አንድ መሆኑ ይታመናል።

ውጫዊ መያያዣ

ለማስተካከል
  • [1] Archived ሴፕቴምበር 1, 2017 at the Wayback Machine Heagy, Thomas C. (2014), "Who was Menes?", Archeo-Nil 24: 59–92 

]