መለጋሲ (Malagasy) ከአውስትሮኔዚያን የቋንቋ ቤተሠብ ቋንቋዎች ሁሉ ምእራበኛው ሲሆን የማዳጋስካር መደበኛ ቋንቋ ነው። 1500-2000 አመታት ከዛሬ በፊት ከእንዶኔዚያ የመጡ የማዳጋስካር ኗሪዎች ቋንቋ በመሆኑ፣ ከቃላቱ መዝገብ 90% ከመቶ በቦርኔዮ እንዶኔዚያ ከተገኘው ቋንቋ ከማአንያን ጋራ ተመሳሳይ ነው። የቀሩትም 10% ቃላት በተለይ ከአፍሪቃ ቋንቋዎች (ከባንቱ) እና ከአረብኛ ተበድረዋል።

በአረፍተ ነገር ውስጥ ግሡ ከሁሉ ይቀድማል። ይህ ተራ እንደ ዕብራይስጥ ይመስላል እንጂ ለብዙዎች ቋንቋዎች የተለመደ አይደለም። በየቃሉ ውስጥ ከመጨረሻው ክፍለ-ቃል በፊት የሆነው ክፍለ-ቃል አናባቢ ይጠበቃል፤ ሌሎቹ አናባቢዎችም ይነበነባሉ (በሙሉ አይስሙም)፤ ስለዚህ "Malagasy" እንደ ፈረንሳይኛ አጻጻፉ "Malgache" (መልሽ) ይመስላል።

ነገር ግን መጨረሻው ክፍለ-ቃል -ka (-ከ), -tra (-ትረ), ወይም -na (-ነ) ሲሆን፣ የተጠበቀው ከመጨረሻው 2 በፊት የሆነው ክፍለ-ቃል ነው። በዚህ መንገድ "fanorona" የሚለው ቃል እንደ "ፈርን" ይመስላል። (በአጻጻፍ ረገድ፣ "o" የሚለው ፊደል እንደ "ኡ" ይመስላል፤ "-i" በመጨረሻ ሲሆን "-y" ይሆናል።)

Wikipedia
Wikipedia