ሆርካም
(ከሖርካም የተዛወረ)
ሆርካም (ወይም ሃር፣ ታርኪም) በጥንታዊ የኢትዮጵያ ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ ከንግሥት ነሕሴት ናይስ ቀጥሎና ከንጉሥ 1 ሳባ አስቀድሞ ለ29 ዓመታት የኩሽ (ኢትዮጵያ) ንጉሥ ነበረ። የነገሠበት ዘመን በየምንጩ የሚለያይ ነው፤ ለምሳሌ በተክለጻድቅ መኩሪያ ዝርዝር ከ2404 እስከ 2375 ዓክልበ. ነበረ። በሌላ ቁጠራ ከ2123 እስከ 2094 ዓክልበ. ነገሠ።
አለቃ ታዬ እንደ ጻፈው ንጉሥ ሃር ሲለው በ15ኛ ዓመቱ በከነዓን አገር ላይ ረሃብ ስለ ጸና ከከነዓን ልጆች የአራዴዎን (አርዋዲ) ልጅ አይነር (ወይም አናየር) እና ሚስቱ ኤንቴላ ከከነዓን ወደ ኩሽ ገቡ። የቅማንት ብሔር ከነርሱ እንደ ተወለዱ ይተረካል።
ቀዳሚው ነሕሴት ናይስ |
የኩሽ ንጉሥ | ተከታይ 1 ሳባ |