ማርስ ወይም ቀይዋ ፈለክ፡ (ምልክት፦♂) መሬት በምትገኝበት ማለትም ሚልክ ዌይ ተብሎ በሚጠራው ረጨት ወይም የከዋክብት ስብስብ ውስጥ የሚገኝ ፈለክ ነው። ይህ ፈለክ ከፀሐይ ባለው ርቀት 4ኛ (አራተኛ) ነው። ከበፊቱ ሜርኩሪቬነስ እና መሬት የተባሉ ፈለኮች ይገኛሉ። ኸበስተኋላው ደግሞ ጁፒተርሳተርንኡራኑስነፕቲዩን እና ፕሉቶ የተባሉት ይገኛሉ።


ይህ ፈለክ በዚህ ረጨት ውስጥ ከሚገኙ ፕላኔቶች በግዝፈቱ የስድስተኛ ደረጃን ይይዛል። እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ህይወት ያለው ነገር ይኖርበታል ተብሎ ሲታመን ቆይቷል። ነገር ግን በቅርቡ የወጡ መረጃዎች ህይወት ያለው ነገር እንዳልተገኘ «ኢኮነም ድሉተ» መሆኑን ያመላክታሉ። በአብዛሃኛው በ ካርቦንዳይኦክሳይድ የተሞላ ቢሆንም በአንጻራዊ ሁኔታ ለ ህይወት ያላቸው ነገሮች ምቹ የሆነ ከባቢ አየር አለው። መጠኑ ከመሬት ያንሳል። በተለምዶ ቀይዋ ፈለክ እየተባለች ትጠራለች

የማርስ ምድር በተንቀሳቃሽ ሮቦቶች ፎቶ እንደተነሳ