ከ«ውክፔዲያ ውይይት:የአርዕስትና የስም አጻጻፍ ልምድ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
መስመር፡ 38፦
 
:«ሥራ» ለግዕዝ አጻጻፍ ትክክለኛ ቢሆንም በአማርኛም የተሻለ ወይም የተመረጠ ቢሆንም፣ «ስራ» እንደ ስኅተት እንደሚቆጠር አይመስለኝም። ሁለቱ ሲፈራረቁ ብዙ ጊዜ በተከበሩ ህትመቶችም ሲታዩ ተራ ነገር ነው። ስለዚህ አዛጋጆች እዚህ ሲጽፉ፣ ሁለታቸውን የምንቀብል ብንሆን እንደሚሻል እገምታለሁ። ነገር ግን አንድ ቃል ወደ ተሻለው ወይም ወደ ተመረጠው ወይም ወደ ግዕዙ አጻጻፍ ለማስተካከል የሚፈልግ አዛጋጅ ቢኖር ይህ ደግሞ መልካም ነው። ለመሆኑ ለመጣጥፉ አርዕስት ከአንዱ ወደ ሌላው አጻጻፍ መምሪያ መንገድ ለመፍጠር ቀላል ነገር ነው! [[User:Codex_Sinaiticus|ፈቃደ]] ([[User talk:Codex_Sinaiticus|ውይይት]]) 14:25, 10 ፌብሩዌሪ 2008 (UTC)
 
ፈቃደ፣ በተቻለ መጠን የአማርኛ ቃላት በትክክለኛ ፊደላት መጻፍ ይኖርባቸዋል። በእርግጥ ለአንዳንዶቻችን ለቃላት የትኛውን ፊደል በትክክል መምረጥ ያስቸግራል። ሆኖም ለምሣሌ በ"ፀሐይ" ፋንታ "ጸሀይ" ወይም በ"ዓለም" ፋንታ "አለም" ወይም በ"ንጉሥ" ፋንታ "ንጉስ" ፣ ወዘተረፈ፣ ሆኖ ሲጻፍ ለአንባቢ ዓይን እና መንፈስ አጸያፊ ነው። አንተ ፊደላት "ሲፈራረቁ ብዙ ጊዜ በተከበሩ ህትመቶችም ሲታዩ ተራ ነገር ነው" ብለሃል። በእኔ አስተያየት ግን ዊኪፔድያ ላይም ሆነ በሌላ ጽሑፍ መልክ የግዕዝ ፊደላችንን ማጠንከር እንጂ በቸልተኝነት'ማ እነዚያ 'የተከበሩ' ያልካቸው የጀመሩትን የቋንቋ አዳካሚነት መንገድ መከተል ነው።--[[User:Bulgew1|Bulgew1]] 10:26, 26 ኤይፕርል 2008 (UTC)
Return to the project page "የአርዕስትና የስም አጻጻፍ ልምድ".