ሉድ (ዕብራይስጥלוּד) በኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 10 መሠረት የሴም ልጅ የኖህም ልጅ ልጅ ነበረ። ይህ ሉድ (የሴም ልጅ) እና ምጽራይም የወለደው ሉዲም ግን ሁለት የተለያዩ ዘሮች ሆነው ይቆጥራል።

የሉድ ተወላጆች በዮሴፉስና በሌሎች ጸሐፍት ዘንድ የትንሹ እስያ ሀገር ልድያ (አካድኛሉዱ) ሆኑ። ከልድያም አስቀድሞ በዚያ ዙሪያ ሉዊያ የተባለ አገር ነበር። በመጽሐፈ ኩፋሌ ድግሞ የሉድ ርስት 'የሉድ ተራሮች' (ከአራራት ወደ ምዕራብ፣ በትንሹ እስያ) ናቸው። ከዚህ በላይ የግሪክ ታሪክ ጸሐፊ ሄሮዶቶስ እንዳለ፣ ልድያ ከንጉሳቸው ከሉዶስ (Λυδός) ተሰየመች። የአቡሊድስ ዜና መዋዕል (226 ዓ.ም. ገደማ) የሉድ ልጆች 'ላዞኔስ' ወይም 'አላዞኒ' (ሓሊዞናውያን) ሲለን፣ ስትራቦን ሐሊዞናውያን በሐሊስ ወንዝ ላይ ኖሩ በማለት አገኛቸው። ሆኖም በአቡሊድስ ዘንድ፣ «ልድያ» የተባለች አገር ከሉዲም ምጽራይም ወጣች።

እስላም ታሪክ ጸሃፊ ሙሐመድ እብን ጃሪር አል-ታባሪ 907 ዓ.ም. ገደማ በጻፈው ታሪክ የሉድ ሚስት የያፌት ልጅ ሻክባህ ስትሆን የፋርስና የጅዮርጅያ ዘሮች እንዲሁም ሌሎች የምሥራቅ ሕዝቦች ወለደችለት ይላል።