የሕግ የበላይነት
(ከየህግ የበላይነት የተዛወረ)
የሕግ የበላይነት ማለት ማናቸውም ሰው ወይም ወኪል በሕጋዊ መሠረት ከሆነ ከሕግ ሥር ተጠቅልሎ ይገኛል። የመንግስት ውሳኔዎች ከታወቁት ሕጋዊና ግብረገባዊ መርኆች ይደርሳሉ የሚል ጽንሰ ሀሣብ ነው። ከሕጉ በላይ የሆነ የለም ይላል። የሕገ መንግሥት ታሪክ እንዳሳየን ይህ መርኅ ከጥንት ጀምሮ ታውቋል። አሪስጣጣሊስም እንደ ጻፉ፣ «ከዜጎች ማንም ሰው ከመግዛት ይልቅ ሕጉ እንዲገዛ ይገባል።»