ሐመልማል አባተኢትዮጵያ ታዋቂ ድምፃዊ ስትሆን ብዙ ዘመናዊ የሙዚቃ ስራዎችን በማቅረብ ትታወቃለች።

ሐመልማል አባተ

የህይወት ታሪክ

ለማስተካከል

ሐመልማል ያደገችው አሰበ ተፈሪ ሲሆን ሙያዋን የጀመረችው በቤተ ክርስትያን ዘማሪ ሆና ነው።[1] የመጀመሪያው አልበሟ የወጣው በ፲፱፻፸፮ ዓ.ም. ነው።[1]

ሐመልማል አባተ የሁለት ሴት ልጆች እናት ናት።[2][3]

ግንቦት ፲፫ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. በመካኒሳ መንገድ አቦ ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ የሚገኘው የአርቲስት ሐመልማል ቪላ ቤት በእሳት ቃጠሎ የወደመ ሲሆን የቃጠሎው መንስኤ ወደ ቤቱ የሚመጣው የኤሌክትሪክ ኃይል ከፍተኛ መዋዠቅ እንደሆነ ይጠቀሳል።[4]

ከድምፃዊነትም አልፎ ሐመልማል የራሷን የሙዚቃ አሳታሚ ድርጅት አመል ፕሮዳክሽንስ በሚል ስም አቋቁማለች።[2] ከሙዚቃ ሥራ በተጨማሪም ሐመልማል በንግድ ዘርፍ በግንባታ ስራ እንዲሁም አመል ካፌ ተሞክሮ አላት። [3]

የስራ ዝርዝር

ለማስተካከል

ማጣቀሻዎች

ለማስተካከል
  1. ^ Jossy In Z House
  2. ^ አዲስ አድማስድምፃዊ ሐመልማል አልበም አሳተመች የሞሃ ፔፕሲ ለአልበሙ ከግማሽ ሚ. ብር በላይ አውጥቷል
  3. ^ ኢ.ቢ.ኤስ. ቴሌቪዥን «እንጫወት» ዝግጅት፣ ሐመልማል አባተ ቃለ መጠይቅ
  4. ^ Awramba Times፣ የአርቲስት ሐመልማል አባተ ቪላ በእሳት ቃጠሎ ወደመ