አዋሳ ከአዋሳ ሃይቅ በታላቁ ሪፍት ቫሌ/ስምጥ ሸለቆ ላይ የሚገኝ ከተማ ነው። የደቡብ ሕዝቦች ክልል ዋና ከተማ ስትሆን በሲዳማ ዞን ተገኛለች። የአዲስ አበባ-ናይሮቢ መንገድ ላይ በላቲቱደና ሎንጁቱድ 7°3′ ሰሜን ኬክሮስ እና 38°28′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ናት። አዋሳ በውበትዋና በትልቅነትዋ ባሁኑ ጊዜ ታላቅ የቱሪስት መስህብ ያላት ነች።

በማዕከአዊ ስታቲስቲክ ባለስልጣን ትመና የ119,623 ሰው መኖሪያ ስትሆን ከነሱም 60,378 ወንዶች 59,245 ሴቶች ሆነው ተተምነዋል። አዋሳ የቀድሞ ሲዳሞ ክፍለ ሓገር ዋና ከተማ የነበረች የደቡብ ዩኒቨርሲቲ፥ የአንድ ኤርፖርትና የሰፊ ገበያ ማዕከል ናት። አዋሳ ከ1998 ዓ.ም. ጀምሮ ሃዋሳ በመባል የታወቃል። ይህን ተመርክዞ የደቡብ ዩኒቨርሲቲ ሃዋሳ በመባል ስሙ ተቀይሮአል።

የሃዋሳ ከተማ በአሁን ሰዓት በከፍተኛ ደረጃ እያደገች ያለች ከተማ ሰትሆን ወደ 600,000 ነዋሪ እንደሚገኝባት ይገመታል። ከተማዋን በሰሜን ኦሮምያ በደቡብ ዲላ በምዕራብ ከምባታ በ ምስራቅ አለታ ወንዶ ያዋስኑዋታል።


አሁን በሲዳማ ክልል