2 ፑዙር-አሹርአሹር ንጉሥ ነበር። ምናልባት 1790-1782 ዓክልበ. አካባቢ ገዛ። የ1 ሳርጎን ልጅና ተከታይ ይባላል።

ሃቲ የነበሩት ካሩም (የንግድ ጣቢያዎች) አስቀጠለ፤ እንዲሁም የከተማው ግድግዳ ታድሶ እንዳሠራ ከጽላቶቹ ይታወቃል። ልጁ ናራም-ሲን ተከተለው። ብዙ ሌላ መረጃ አይታወቅም።

የዓመት ስሞች

ለማስተካከል

የያንዳንዱ አሦራዊ ዓመት ስም ለዚያ ዓመት የተሾመው የሊሙ ስም ነበረ። ከዚህ በታች የዓመቱ ሊሙ እና የሊሙ አባት ስም እንደ ኡልትራ አጭር አቆጣጠር ይዘርዝራሉ።[1]

1790 ዓክልበ. - አሹር-ኢዲን፤ ሹሊ ልጅ
1789 ዓክልበ. - አሹር-ናዳ፤ ፑዙር-አና ልጅ
1788 ዓክልበ. - ኩቢያ፣ ካሪያ ልጅ
1787 ዓክልበ. - ኢሊ-ዳን፣ ኤላሊ ልጅ
1786 ዓክልበ. - ጺሉሉ፣ ኡኩ ልጅ
1785 ዓክልበ. - አሹር ናዳ፣ ኢሊ-ቢናኒ ልጅ
1784 ዓክልበ. - ኢኩፒ-ኢሽታር፣ ኢኩዋ ልጅ
1783 ዓክልበ. - ቡዙታያ፣ ሹሉ ልጅ
1782 ዓክልበ. - ኢናያ፣ አሙራያ ልጅ
ቀዳሚው
1 ሳርጎን
አሹር ገዥ
1790-1782 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ናራም-ሲን
  1. ^ የመስጴጦምያ ነገሥታት (ፈረንሳይኛ)