2 ኤፓርቲ
2 ኤፓርቲ ከ1858 እስከ 1838 ያሕል የኤላም («አንሻንና ሱስን») ንጉሥ ነበር። የኤፓርቲ ሥርወ መንግሥት መሥራች እንዲሁም የሲማሽኪ ሥርወ መንግሥት ፱ኛ ንጉሥ ይቆጠራል። ብዙ ሌላ ዝርዝር ስለዚህ ንጉሥ አይታወቅም፣ ግን አንድ የዓመቱ ስም ብቻ ሲታወቅ እርሱ «(አምላኩ) ኤፓርቲ ንጉሥ የሆነበት ዓመት» ተባለ። ከዚህ ጊዜ በቀር ግን እላማዊ ንጉሥ እራሱን «አምላክ» ሲል በታሪክ ሰነዶች አይገኝም።
ልጁ 1 ሺልሐሐ የሱስን አገረ ገዥ ተደረገና ከአባቱ ቀጥሎ ወደ ዙፋኑ ተከተለው። ሴት ልጁ ደግሞ ከዚህ በኋላ የሱስን ገዥ ሆነች፤ ስሟም ባይታወቅልንም በኋለኛ ትውልድ እንደ ክቡር ወላጅ እንደ ከበረች ይታወቃል።