1 ኤሪክስዊድን አፈ ታሪክጎታውያን ንጉሥ ነበረ። በ1546 ዓ.ም. በኡፕሳላ ኤጲስ ቆጶስዮሓንስ ማግኑስ በታተመው የስዊድን ታሪክ መጽሐፍ እንደሚለው፣ 1 ሲጎ በስዊዶች ላይ እየነገሠ ኤሪክ በጎታውያን ነገድ ላይ ተመረጠ፤ ለ68 ዓመታት (2201-2133 ዓክልበ. ገደማ) እንደ ነገሠ ይባላል። ይህ ኤሪክ የ1 ጌጣር (ጎጉስ) ልጅ ወይም ልጅ-ልጅ ነበረ። ሕግጋትን አወጣ፤ ግዛቱንም በሩቅ አገራት አስፋፋ፤ ሰውም ገና ወደማይኖርበት ወደ «ቬታላ» (የአሁኑ ዴንማርክ) ሰፈረኞችን ሰደደ። ስለዚሁ ድርጊት ማግኑስ «የኤሪክ ዘፈን» የተባለውን ድርሰት በሮማይስጥ አሳተመ። በማግኑስ ዘንድ፣ ከኤሪክ ዘመን በኋላ ግን ጎታውያን ጣኦታትን ተከተሉ፤ ዴንማርክና ስዊዶችም ለ660 ዓመታት ያህል በፈራጆች ተገዙ።