1 አሹር-ራቢአሦር ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ በ1451-1441 ዓክልበ. ገደማ የአሦር ንጉሥ ነበረ። ስንት ዓመት እንደ ገዛ ከሰነዱ ጠፍቷል።

ቀዳሚው አሹር-ሻዱኒ የወንድሙ ኑር-ኢሊ ልጅና ወራሽ ነበር። አሹር-ሻዳኒ አንድ ወር ብቻ ከገዛ በኋላ አጎቱ የ1 ኤንሊል-ናሲርም ሁለተኛው ልጁ 1 አሹር-ራቢ ዙፋኑን ከአሹር-ሻዱኒ በመንፍቅለ መንግሥት ያዘው ይላል።

ልጁ 1 አሹር-ናዲን-አሔ ተከተለው።

ቀዳሚው
አሹር-ሻዱኒ
የአሦር ንጉሥ
1451-1441 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
1 አሹር-ናዲን-አሔ