1 ቡርና-ቡርያሽ
1 ቡርና-ቡርያሽ ከ1483 እስከ 1473 ዓክልበ. ግድም ድረስ የባቢሎን (ካራንዱኒያሽ) ካሣዊ ንጉሥ ነበረ።
«የወቅቶች ሥመራ ዜና መዋዕል» (ABC 21) በተባለው ጽላት ይጠቀሳል፦
- «የአሦር ንጉሥ ፑዙር-አሹር (1499-1476 ዓክልበ. ገደማ) ና የካርዱኒያሽ (የካሣውያን ባቢሎን ግዛት) ንጉሥ ቡርና-ቡርያሽ መሓላ ገብተው ይህኑንም ድንበር ወስነው ተስማሙ።»
የቡርና-ቡርያሽ ተከታይ 3 ካሽቲሊያሽ ልጁ ነበር። ሌላው ልጁ ኡላም-ቡርያሽ ከነርሱም ተከተላቸው። ስሙ «ኡላም-ቡርያሽ የቡርና-ቡርያሽ ልጅ» በሚሉ አንዳንድ ቅርሶች ላይ ተገኝቷል። ባለፈውም ቅርብ ጊዘ ውስጥ (2005 ዓም ግድም) ለሌላ ልጁ «ካሽቲሊያሽ የቡርና-ቡርያሽ ልጅ፣ የአጉምም ልጅ ልጅ» የሚል ጽላት ተገኝቷል። ከዚህ 2 አጉም የቡርና-ቡርያሽ አባት ይመስላል።
ቀዳሚው 2 አጉም |
የባቢሎን ንጉሥ 1483-1473 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ 3 ካሽቲሊያሽ |