ፍድቀል
ፍድቀል (Fidchell) ሠንጠረዥን የመሰለ የጥንታዊ አይርላንድ ጨዋታ ነበር። ተመሳሳይ ጨዋታ በዌልስ ጒድብወል ተባለ።
ፍድቀል የሚታወቀው በተለይ ከሥነ ጽሑፍ ጥቅሶች ሲሆን የጨወታው መልክ ወይም ደንቦች በትክክል እርግጠኛ አይደሉም። ከነዚህ ፍንጮች አሁን ስለ ፍድቀል አጨዋወት በርካታ ልዩ ልዩ አስተሳስቦች አሉ።
ባብዛኞቹ ግመቶች ዘንድ የአንዱ ወገን ንጉሥ በሠንጠረዡ መካከል በመቆም ይጀምራል። ከእርሳቸው መሃል ሌሎች የሚከለከሉ ክፍሎች አሉ። የሌላው ወገን ክፍሎች በሠንጠረዡ ዳሮች ይጀምራልሉ፣ እነርሱ ንጉሡን ለመክበብ እየሞከሩ ንጉሡ ግን ወደ ማዕዘን በመድረስ ያሸንፋል።
በትውፊቶቹ ዘንድ ይህ ጨወታ በሉግ (ምናልባት 15ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ.) ተፈጠረ፤ ታምራዊ የነገሥታት ጨወታ ሲሆን አጨዋወቱ በውግያ ውጤት ላይ ተጽእኖ እንደ ነበረው በትውፊቶቹ ይጻፋል። በአንዱም ትውፊት በራሳቸው በቀጥታ የሚንቀሳቀሱ ክፍሎች የነበሩት ታምራዊ የፍድቀል ሠንጠረዥ ተገኘ። የፍድቀል ትርጉም «የእንጨት ጥበብ» ቢሆን በብዙ ትውፊቶች ክፍሎቹ ከወርቅና ብር እንደ ተሠሩ ይባላል።
በሥነ ቅርስ አንዳንድ የሠንጠረዥ ሠሌዳ ሲገኝ ሊቃውንቱ ግን የትኛው የጨወታ አይነት እንደ ጠቀመው በእርግጥ ሊያውቁ አይችሉም።