ጻላጊኛ (ᏣᎳᎩ ᎦᏬᏂᎯᏍᏗ /ጻላጊ ጋዎኒሂስዲ/) በጻላጊ ብሔር የሚነገር በተለይ በአሜሪካ ኖርዝ ካሮላይና እና ኦክላሆማ ክፍላገራት የሚሰማ ቋንቋ ነው። የኢሮኳዊ ቋንቋዎች ቤትሠብ አባል ነው።

ጻላጊኛ ፊደል ካርታ

በራሱ ጻላጊኛ ፊደል ይጻፋል። ይህ ፊደል ሰኰያ በተባለ የጻላጊ ሊቅ በ1817 ዓም. ግድም ተፈጠረ።

በጻላጊኛ የምላስ ውልብልቢት በታችኛ ጥርስ ግርጌ ይቀመጣል እንጂ እንደ አማርኛ በላይኛ ጥርስ አይደለም።

«ትላ፣ ትሌ፣ ትሊ፣ ትሎ፣ ትሉ፣ ትለን» የሚሉ ፊደላት ደግሞ እንደ «ህላ፣ ህሌ...»፣ «ቅላ፣ ቅሌ...»፣ «ጥላ፣ ጥሌ» ወዘተ. ያሰማሉ።

«ጻ፣ ጼ...» ወዘተ. ደግሞ እንደ «ጃ፣ ጄ...»፣ «ቻ፣ ቼ...» ያሰማሉ። ምሳሌ፦ ᏣᎳᎩ /ጻላጊ/፣ /ጃላጊ/፣ /ቻላጊ/...።

«ህ»፣ «ዕ»፣ «እ» የሚሉ ድምጾች ብዙ ጊዜ በጽሕፈት ባይጻፉም በአጠራር በሰፊ ይጨመራሉ።

ᏣᎳᎩ: ᏂᎦᏓ ᎠᏂᏴᏫ ᏂᎨᎫᏓᎸᎾ ᎠᎴ ᎤᏂᏠᏱ ᎤᎾᏕᎿ ᏚᏳᎧᏛ ᎨᏒᎢ. ᎨᏥᏁᎳ ᎤᎾᏓᏅᏖᏗ ᎠᎴ ᎤᏃᏟᏍᏗ ᎠᎴ ᏌᏊ ᎨᏒ ᏧᏂᎸᏫᏍᏓᏁᏗ ᎠᎾᏟᏅᏢ ᎠᏓᏅᏙ ᎬᏗ.[1]
ጻላጊኛ፦ ኒጋዳ አኒየንዊ ኒጌጉዳዕለና አሌ ኡኒህሎዪ ኡናዴህና ዱዩክደን ጌሰንኢ። ጌጂኔላ ኡናዳነንቴህዲ አሌ ኡኖህሊስዲ አሌ ሳግዉ ጌሰን ጁኒለንዊስዳኔዲ አናህልዲነንድለን አዳነንዶ ገንህዲ።[1]
አማርኛ፦ የሰው ልጅ ሁሉ ሲወለድ ነጻና በክብርና በመብትም እኩልነት ያለው ነው። የተፈጥሮ ማስተዋልና ሕሊና ስላለው አንዱ ሌላውን በወንድማማችነት መንፈስ መመልከት ይገባዋል። (--አንቀጽ ፩ ከ«የሰብዓዊ መብት አቀፋዊ መግለጽ»)[1]

ደግሞ ይዩ

ለማስተካከል
  1. ^ "Cherokee syllabary" (1998–2009). በMay 14, 2009 የተወሰደ.