|
|
|
ግቤት x ከ ነጥብ c በ δ ርቅት ላይ ካለ, የf(x) ዋጋ ከጥጉ L በ ε ርቀት ውስጥ ይገኛል። .
|
|
ለማናቸውም x > S, አስረካቢ f(x) ከጥግ L በ ε ርቀት ውስጥ ይገኛል
|
አስረካቢ f(x) እና ነጥብ c ቢሰጡ፣ አስረካቢው በተሰጠው ነጥብ ላይ ሊኖረው የሚችለው ጥግ እንዲህ ይጻፋል
-
ትርጉሙም xን ወደ ነጥብ c በማስጠጋት የ አስረካቢ f(x) ዋጋን በተፈለገ መጠን ወደ L ማስጠጋት ይቻላል። እንግዲህ " የx ዋጋው ወደ c ሲጠጋ, የf ጥግ L" ነው ይባላል። በጥንቃቄ መታየተ ያለበት፣ በአንድ ነጥብ ላይ አንድ አስረካቢ ያለው ጥግ እና ውጤት አንድ ላይሆኑ ይችላሉ፣ ማለት f(c) ≠ L። እንዲያውም አስረካቢ f(x) በነጥብ c ላይ ትርጉም ላይኖረውም ይችላል። ጥግ፣ አስረካቢው የሚቀርበውን ዋጋ እንጂ የአስረካቢውን ዋጋ አያሰላም።
-
እዚህ ላይ f(1) በዜሮ ማካልፈል ስለሚሆን አስረካቢው 1ን ማስረከብ አይችልም። በሌላ አነጋገር አስረካቢው 1 ላይ ትርጉም የለውም። ሆኖም ግን x ወደ 1 እየተጠጋ ሲሄድ, f(x) ወደ 2 እየተጠጋ ይሄዳል።
ከላይ የተሰጠውን በስራ ለማሳየት መጀመሪያ x^2-1 መተንተን ያስፈልጋል. [(x-1)(x+1)]/(x-1). ከዛ መጣፋት የሚችሉትን ካጣፋን በሓላ x+1 ይቀራል. በመጨረሻም 1ን በx ቦታ መተካት. ስለዚህ መልሳችን 2 ነው ማለት ነው.
f(x)=(2x-1)/x, x-->∞ ከላዪም ከታችም ∞ን ስለሚተጋ -1 ለውጥ አያመታም. ስለዚህ xን በx አጣፍተን መልሳችን 2 ይሆናል ማለት ነው.
f(0.9) |
f(0.99) |
f(0.999) |
f(1.0) |
f(1.001) |
f(1.01) |
f(1.1)
|
1.900 |
1.990 |
1.999 |
⇒ ትርጉም የለሽ ⇐ |
2.001 |
2.010 |
2.100
|
ከሰንጠረዡ መረዳት እንደሚቻለው xን ወደ 1 በማስጠጋት አስረካቢ f(x)ን ወደ 2 በፈለግነው መጠን ማስጠጋት ይቻላል። ስለሆነም አስረካቢው በ1 ላይ ያለው ጥግ 2 ነው ይባላል።
ሂሳባዊ የቀኖና ትርጉም
Edit
አስረካቢው f(x) በc ላይ ጥግ አለው ሲባል በሂሳብ ቋንቋ እንዲህ ይጻፋል፡
-
|
|
የጥግ ቀኖናዊ ትርጉም
|
የጥግ ባህሪዎች
Edit
- እኩልዮሽ
-
- መደመር
-
- መቀነስ
-
- ማባዛት
-
- ማካፈል
-