ግዕዝኤዲት (GeezEdit) የኢትዮጵያ ኮምፕዩተሮችና ሶፍትዌር ከኣቀረባቸው የተለያዩ ፕሮግራሞች ኣንዱ ነው። ግዕዝኤዲት ለመጀመሪያ ጊዜ ለገበያ የቀረበው እ.ኤ.ኣ. በ1994 ነው።

ግዕዝኤዲት ነፃ መክተቢያ ለማስተካከል

ነፃ የአማርኛ መክተቢያ የማንንም ፈቃድና ዕርዳታ ሳይጠየቅ ግዕዝን በዊንዶውስ እና ማክ ኮምፕዩተሮች መክተብ ያስችላል። ለምሳሌ ያህል http://freetyping.geezedit.com Archived ዲሴምበር 4, 2020 at the Wayback Machine ድረ ገጽ ሄዶ «ግዕዝኤዲት» የሚለውን ቃል ከትቦና ቀድቶ (ኮፒ) ቃሉን የውክፔዲያ መፈለጊያ ውስጥ በመለጠፍ (Paste) በዓማርኛ መፈለግ (Search) ይቻላል።

ኣንድ ሌላ ቦታ የተጻፈ የዓማርኛ ጽሑፍ ኮፒ ኣድርጎ የግዕዝኤዲት መክተቢያ ገጽ ላይ በመለጠፍ ጽሑፉን ማረምና ማሻሻል ይቻላል። ይህ ፕሮግራም በነፃ በተሰጠበት ኣራት ዓመታት ውስጥ ከ፩ ሚሊዮን ጊዜ በላይ በተጠቃሚዎች ተከፍቷል። ጽሑፉንም በኢ-ሜይል ለእራስ በመላክ በእጅ ስልክ ማንበብ ስለሚቻል ዓማርኛውን በላቲን ፊደል ከመጻፍ ይገላግላል። እንዲህም ሆኖ ብዙ ኢትዮጵያውያን ገጹን ለማያውቁት ስለማያስተዋውቁ ድርሻዎቻቸውን እንዲወጡ ግንዛቤ ማስጨበጥ ኣንዳስቸገረ ቆይቷል። ግዕዝ ኮምፕዩተራይዝድ ሲደረግ የተከተበው በሁለት መርገጫዎች ነበር። ስለዚህ ማንኛውንም የግዕዝ ቀለም በሦስት መርገጫዎች መክተብ ነውር ነው። ምክንያቱም ሁሉንም የግዕዝ ቀለሞች እንደ ላቲኑ መክተቢያ በኣንድና ሁለት መርገጫዎች መክተብ ስለተቻለ ልንደሰትና ፊደላችንን ለዓለም የምናስተዋውቅበት ጊዜው ኣሁን ስለሆነ ነው።

የነፃው ድረገጽ ኣንዱ ትልቅ ጥቅም በቤተ መጽሓፍት ኮምፕዩተሮች ዓማርኛ ጽሑፎችን ለመፈለግና ለማተም ነው። [1]

ግዕዝኤዲት ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ በኣደረጉት በዶ/ር አበራ ሞላ የተፈጠረ ኣዲስ የግዕዝ መክተቢያ ነው። በእዚህ አዲስ ዘዴ እያንዳንዱ የግዕዝ ቀለም የሚከተበው በአንድ ወይም ሁለት መርገጫዎች ብቻ ነው። [2] ግዕዝኤዲት ቪድዮም እዚህ አለ። [3] የግዕዝኤዲት ኣከታተብ የመጀመሪያውን የባለቤትነት መብት ቍጥሩ 9,000,957 የዩናይትድ እስቴትስ ፓተንት ኣግኝቷል። [4]

ግዕዝኤዲት ለዊንዶውስ ለማስተካከል

ለማይክሮሶት ዊንዶውስ ለእክስፒ እስከ ዊንዶውስ 10 ጋር የሚሠራ እዚህ ኣለ። [5]

ግዕዝኤዲት ለእጅ ስልኮች ለማስተካከል

ለኣፕል ኣይፎን የእክ ስልክና ኣይፓድ ከዊንዶውስ ጋር ኣንድ ዓይነት በሆነው ኣከታተብ የሚሠራ ኣለ።

ግዕዝኤዲት ለኣንድሮይድ የእጅ ስልክ ለማስተካከል

 
ግዕዝኤዲት ለኣይፎን ፳፻፯ ዓ.ም.

የውጭ መያያዣዎች ለማስተካከል