ጉንጉን (የቻይና)
ጉንጉን የጽጉር አሠራር አይነት ሲሆን ይህ ቄንጥ በቻይና ታሪክ ከ1611 እስከ 1904 ዓ.ም. ድረስ ለቻይናዊ ወንድ ሁሉ ግዴታ ሆነ።
የማንቹ ሕዝብ ወገን አገሩን ወርረው ሲይዙ፣ በቻይና ክፍሎች ውስጥ የማንቹዎቹን ልማዳዊ ጽጉር አሠራር በተገዙት ሕዝቦች ላይ ከ1611 ዓ.ም. ጀምሮ አስገደዱ። ይህም ማለት ጽጉሩን ከፊት በየአሥሩ ቀኖች መላጭ፤ በኋላም ረጅም የማይቋረጥ የተጐነጐነ ሹሩባ መኖር አስፈላጊ ሆነባቸው።
ከቻይና ሕዝብ መካከል አብዛኞቹ ይህንን ፈላጭ ቁራጭ ድንጋጌ ሳይቀበሉ እምቢ ብለው ማንቹዎቹ በ1637 ዓም በሞት ቅጣት ግዴታዊ አደረጉት። የቻይና ሕዝብ በኮንግ-ፉጸ እምነት መርኆች እኛ ራሳችንን አንጐዳም አሉ። ስለዚህ ብዙዎቹ በጀግናነት በመታገል ደማቸውን ፈሰሱ። የቻይና ሕዝብ ቁጥር ከ51 ሚሊዮን በ1612 ዓም እስከ 20 ሚሊዮን በ1643 ዓም ተቀነሰ። የቻይና ሰዎች እንደ ተባሉ ወይም ጽጉሩ ወይም ራሱ ይቋረጥ።
በ1904 ዓም በሢንኃይ አብዮት ዘመን የቻይና ሕዝብ አንድላይ ጉንጉናቸውን ቈረጡ።