ጅሩ የሚባለው የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ሕዝቦች የሚኖሩበት በሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኝ አካባቢ ሲሆን በዚሁ ዞን ሁለት ወረዳዎች እና አራት አነስተኛ ከተሞች አሉት። እነሱም እንሳሮና ዋዩ እና ሞረትና ጅሩ ወረዳ ይባላሉ። ጅሩ ከ1680 በፊት "ሸዋ ሜዳ" በመባል ይታወቃል።ጅሩ የሚለውን ስያሜ ያገኘው በኦሮሞ ወረራ ወቅት ስሙን በመቀየር ነበር። ጅሩን ብቻ ሳይሆን ነባር አማራዎችን በማፈናቀል ለሎች የውረሯቸው ቦታዎችም በኦሮሞኛ ስም ተቀይረዋል።በኋላም አማራ መልሶ በ1830 ዓ.ም እርስቱን ሲያስመልስ የቀድሞ የአማርኛ ስሙን ሳይቀይሩ በአዲሱ በተቀየረው ሰም መጠቀም መጀመራቸው በዚህ ጊዜ ስህተት ተፈፀመ።ብዙ አካባባቢዎች በተለይ ደጋማ አካባቢዎች በኦሮሞ አባ ገዳ ስረዓት የሰየሟቸው የኦሮሞ የጎሳ ስም በብዛት ይጠራሉ። ለምሳሌ አልባሳ፣ማንጉዶ፣ጣጢሳ፣በጣሶ፣ጫሶ፣ቦሎ፣ቀርሳ፣የመሳሰሉት የኦሮሞ የጎሳ ስም ናቸው።በሙሉ የተቀየሩት አማራ ከግራኝ ጋር ጦርነት ላይ በነበረበት ወቅት የግራኝ ወረራን ተከትለው በመጡ ዳግም ወረራ የተቀየሩ ናቸው።በሲያደብር ወረዳም በተመሳሳይ ያለ ችግር ሲሆን አብዛኛው በኦሮሞ የጎሳ ስም የሚጠሩ ናቸው። ለምሳሌ ኤጀርሳ ቁበቲ፣ዳዎ ኮምቤልቻ፣አርጎ ወርዮ፣አባያ፣ሮሜ፣ጋመኛ፣መናላፍቶ፣ወሌ፣ርቅቻ ወዘተ የተቀየሩት የግራኝ ወረራን ተከትሎ በመጡት የኦሮሞ ዳግም ወረራ ወቅት እንጂ የቀድሞ ስማቸው አማርኛ ነበር።ይህ ደግሞ ማረጋገጫው አማራ ከግራኝ ወረራ ለመዳን ወደ ቆላ አማራ አካባቢ መሽጎ ነበር ።በወቅቱ ግራኝም ቆላ አካባቢ ወርዶ አማራን ለመውጋት ስላልቻለ ቆላማ አካባቢዎች አልደረስም አማራ እንደያዛቸው ነው።ለምሳሌ ያህል ጎዘጎዛ፣አጥነት፣ታቦት ዋሻ ፣ጎተት ቆላ ፣ላም ዋሻ ፣ላም ገኖ፣አርስ አምባ፣ሞረት፣አመድ ዋሻ፣ ወዘተ አማርኛ ስሞች ናቸው።

  • እንሳሮ እና ዋዩ ወረዳ ዋና ከተማው ደነባ ይባላል። ደነባ ከአዲስ አበባ በ175 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ስትገኝ ከደብረ ብርሃን 45 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች። በዚሁ ወረዳ ለሚ የምትባል አነስትኛ ከተማ አለች።
  • ሞረት እና ጅሩ ወረዳ ዋና ከተማው እነዋሪ ይባላል። እነዋሪ ከአዲስ አበባ በ196 ኪሎ ሜትር ሲርቅ ከደብረብርሀን 66 ኪሎ ሜትር ከደነባ 21 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚገኝ ሲሆን በዚሁ ወረዳ ጅሁር የምትባል ትንሽ ከተማ አለች።

ጅሩ የሚባለው ዞን ከሰሜን መንዝ ፣ ከምስራቅ ተጉለት ፣ ከምእራብ ሰላሌ ፍቼ ፣ ከደቡብ ፣ የኦሮሞ ዞን መንዲዳ ፣ ያዋስኑታል። ይህ ዞን በባህላዊ አስትራረስ ከ200 አመት በላይ በማስቆጠር በዩኔስኮ ተመዝግቧል። በአጠቃላይ ጅሩ የሚባለው በእርሻ እና በከብት ማድለብ ከሚታወቁት ክልሎች አንዱ ነው። ጅሩ የኢትዮጵያ ብሔር ነው።