ጀስትን ቢበር
ጀስትን ድሩ ቢበር (Justin Drew Bieber; ተወለደ ማርች ፩፣ ፲፱፺፬) ነው ካናዳዊ የፖፕ እና የአርኤንድቢ ዘፋኝ።
የመጀመሪያ አልበሙ ማይ ዎርልድ 2.0 (፳፻፪) አስገኘለት የገበያ ስኬት የተቀመጠ አንደኝነት ላይ ከቢልቦርድ ፪፻ አልበሞች፤ ጀስትንን ያደርገዋል በጣሙን ወጣት የደረጃ ሰንጠረዡ ላይ ለመውጣት በ፵፯ አመታት ውስጥ። አልበሙ ያካትታልም በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያገኘውን ነጠላ "ቤይቢ" ይህ ነጠላ ሆኗል ከምንጊዜም ከፍተኛ ከተመሰከሩ ነጠላዎች አንዱ በአሜሪካ። ሁለተኛ አልበሙ አንደር ዘ ሚስትልቶው (፲፻፫) ፡ የመጀመሪያው የገና አልበም ነበር በወንድ አንደኛ ለመሆን ከቢልቦርድ መቶ አልበሞች። በ፳፻፬፣ በሶስተኛ አልበሙ ብሊቭ ከዳንስ፡ፖፕጋ ተቶከረ ፡ ይህን አልበም ተከትሎም ጀስትን ቢበር ከህዝብ ጋር ያለው ግንኙነት በሻካራ ሁኔታ ተቀየረ በተለያዩ አከራካሪ እና በህጋዊ ጉዳዮቹ ምክኛት (በሁለት ሺ አምስት እና ስድስት አመት ውስጥ) ፡ እንዲያውም ሮልንግ እስቶን የተባለ ታዋቂ የመረጃ ድርጅርት ጀስትን ቢበርን "መጥፎ ልጅ" ብሎ ሰየመው በመጋቢት ሁለት ሺ ስድስት ጉዳዩ። ይሁን እንጂ ከሁለት ሺ ስምንት ጀምሮ ጀስትን ቢበር ተቀዳሚነቱን ለዳግም ህዝባዊ ግንኙነቱ ሲያውል ነበር ፡ ሲያውል ነበር ለአይምሮው ጤንነት። የካቲት ሁለት ሺ ስምንት ጂኪው የተባለ ታዋቂ የመረጃ ተቋም ስለ ጀስትን ቢበር ራስ ማደስ ተነሳሽነት አስመልክቶ ፅሑፍ ይዞ ሊወጣም ችሎ ነበር።
አራተኛ አልበሙ ፐርፐዝ በ፳፻፯ ተለቀቀ አስቀደመ ነጠላ "ዌር አር ዩ ናው"ን ከዲጄ ቡድን ጃክ ዩጋ ፤ ነጠላው "ምርጥ ዳንስ ቅጂ"ን አሸነፈ በግራሚ። ፐርፐዝ አመረተ ሶስት ቁጥር አንድ ዘፈኖቹን "ዋት ዱ ዩ ሚን?"፣ "ሶሪ" እና "ሎቭ ዩርሰልፍ"። በዩናይትድ ኪንግደም ሶስት ዘፈኖችን በተከታታይ ከ፩-፫ በማስመዝገብ በታሪክ የመጀመሪያው አርቲስት ሆነ። በ፳፻፰ እና ፱ መካከል ጀስትን ቢበር የተለያዩ፣ አያሌ ስራዎች በጣምራ ሰራ ስራዎች ይካተታሉ "አይ አም ዘ ዋን" እና "ደስፓሲቶ" አንደኛው አንድ ላይ ከሆነ አንድ ሳምንት በኋላ ሁለተኛው አንደኝነት ላይ ተቀመጠ ከቢልቦርድ። በ"ደስፖሲቶ" ጀስትን አሸነፈ የመጀመሪያውን የላቲን ግራሚ ሽልማቱን። በ፳፻፲፪ ጀስትን ለቀቀ የካንትሪ ስልተ ሙዚቃ ዘፈን "ተን ታውዘንድ አወርስ" አሸነፈም ጥንድ/ቡድን በተሰኘ ፈርጅ ግራሚን። አራተኛ አልበሙን ከለቀቀ አምስት አመት በኋላ ጀስትን በ፳፻፲፪ አምስተኛ አልበሙን በተለየ የሙዚቃ አቀራረብ ለቀቀ ከአልበሙም እነዚህ የአርኤንድቢ ሙዚቃዎች አምስት ውስጥ ሊገቡለት ቻሉ ፡ "የሚ" እና "እንተንሽንስ"።
ጀስትን ቢበር ነው ከአለም ምርጥ ሻጭ የሙዚቃ አርቲስቶች አንዱ ሽጦ ከአንድ መቶ ሀምሳ ሚልየን በላይ ቅጂዎች በአለም። በሶስት የአልማዝ ምስክሮች ተከብሯል በርኮርዲን ኢንደስትሪ አሶስዬን ኦቭ አሜሪካ፣ በዘፈኖቹ-"ቤይቢ"፣ "ሶሪ" እና "ደስፓሲቶ"። አያሌ ሽልማቶችን ሊያገኝ ችሏል ተካተው፦ ሀያ ሶስት የአለም ጊነስ ሪከርድ፣ ሀያ ሶስት የቲን ቾይስ ሽልማቶች፣ ሁለት የግራሚ ሽልማቶች፣ ሀያ የቢልቦርድ ሽልማቶች፣ ስምንት የአሜሪከን ሚውዚክ ሽልማቶች፣ ሁለት የብርት ሽልማቶች፣ አራት የኤምቲቪ ሚውዚክ ቪድዮ ሽልማቶች እና የላቲን ግራሚ ሽልማት። ታይም በአለም ከፍተኛ ተፅእኖ ፈጣሪያን ብሎ ከዘረዘራቸው ሰዎች ውስጥ ጀስትን ቢበር አንዱ ነበር በሁለት ሺ ሶስት። ፎርብስ በጣም ሀይል ያላቸው ብሎ ከዘረዘራቸው ዝነኞች አስር ውስጥ ሊገባም ችሎ ነበር በ፳፻፫፣ ፬፣ እና ፭።