ድግጣ ወይም ዝግጣ (Calpurnia aurea) ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው።

ድግጣ

የተክሉ ሳይንሳዊ ጸባይ

ለማስተካከል

አስተዳደግ

ለማስተካከል

በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር

ለማስተካከል

የተክሉ ጥቅም

ለማስተካከል

ዘሩ በማር ለጥፍ ለተስቦ መጠቀሙ በደብረ ሊባኖስ ዙሪያ ተዘገበ። እንዲህ ያለ ለጥፍ ከክትክታ ዘር ጭምር ለተስቦ ሊሰጥ ይችላል። አንድ ሌላ ዝግጅት ለሆድ ትል፣ ለብርቱ ተቅማጥ ወይም ለአንገት ነቀርሳ ይሰጣል፦ የድግጣ እና የክትክታ ቅጠል፣ የምድር እምቧይና የሉት ሥር፣ የቁልቋልና የቅንጭብ ላፒስ፣ ተደቅቀው በውሃ ይጠጣል።[1]

ፍቼ ወረዳ እንደ ተዘገበ፣ ቅጠል፣ ፍሬውና ዘሩ በምግብ ውስጥ ለውሾች ውሻ በሽታ ለማከም ይሰጣል። የድግጣ ቅጠል ተደቅቆ በውሃ ለልክፈት ወይም ለቁስል ይለጠፋል። ፍሬውም ተደቅቆ ለሆድ ቁርጠት ይበላል።[2]

ዘጌ እንደ ተዘገበ፣ የፍሬው ወይም የቅጠል ዱቄት በማር ወይም በውሃ ለቁርባ ለማከም ይጠጣል።[3]

  1. ^ በደብረ ሊባኖስ ዙሪያ ያለው ሕዝብ መድሃኒታዊ እጾች እውቀናና ጥቅም 1998 ዓም ከጥላሁን ተክለሃይማኖት፣ ሚሩጸ ጊዳይ፣ ግርማይ መድኅን፣ ያለም መኮነን፣ አዲስ አበባ ዩኒቬርሲቴ፣ አክሊሉ ለማ ተቋም
  2. ^ የፍቼ፣ ኦሮሚያ ባህላዊ መድሃኒት ጥናት 2006 ዓም ከዓቢዩ እኒየው እና ሌሎች፣ ጎንደርና አዲስ አበባ ኡኒቨርሲቲዎች ሥነ ፍጥረት ኮሌጆች
  3. ^ የዘጌ ልሳነ ምድር ባህላዊ መድሃኒት ጥናት 1999 ዓም ከጥላሁን ተክለሃይማኖት፣ ሚሩጸ ጊዳይ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ