ዴቪድ ሁም
ዴቪድ ሁም (ግንቦት 7 1711 - ነሐሴ 25 1776) የነበረ የስኮትላንድ ታሪከኛ እና ፈላስፋ ነበር። [1] ሁም በዘመኑ ይታወቅ የነበረው በታሪክ ተመራማሪነት ነበር። የእንግሊዝ ታሪክ የሚሉ ትላልቅ መጻሕፍትን በዘመኑ ደርሶ ለህትመት አብቅቶ ነበር። አሁን ግን ሁም የሚታወቀው በዋና ፈላስፋነቱ ነው።
በፍልስፍና መጽሕፉ ላይ እንደሚያስረዳ ብዙው የሰው ልጅ አምኖ የሚቀበላቸው ነገሮች በ በምክንያት የተደገፉ አይደሉም። ይልቁኑ ከስሜትና ደመነፍስ የሚመነጩ ናቸው። ለምሳሌ አምክንዮ የአንድ ነገር መንስኤ ሌላ ነገር ነው ብሎ አይናገርም። ነገር ግን አንድ ክስተት ሲፈጠርና ከዚያ ቀጥሎ ሌላ ክስተት ሲፈጠር ስናይ የመጀመሪያው ክስተት ለሚቀጥለው ክስተት መንስኤ ነው ብለን በ"ስሜት" እንደመድማለን። በተመሳሳይ አንድ ሰው ሰናይ ግለሰብ እንደሆነ ምክንያት አይነግረንም። ይልቁኑ ያ ሰው ደግና ተግባቢ ሆኖ ስናየው በስሜት ሰናይ ነው እንላለን። እኒህ ነገሮች ከምክንያት አይመነጩም ብሎ ሁም ስለሚያምን ተጠራጣሪ ወይንም ኢ-ምክንዮት ፈላስፋ ተብሎ ይታወቃል።
ሁም ሃይማኖት ላይም ተጠራጣሪ ነበር[1]። ሁም ሃይማኖተኛ ሰው አልነበረም። በተአምራትም አያምንም ነበር።
የሁም ዋና ዋና መጻሕፍት
ለማስተካከል- A Treatise of Human Nature: Being an Attempt to introduce the experimental Method of Reasoning into Moral Subjects.[1] (1739-40)
- በዚህ መጽሐፍ፣ ሁም ስለ ሰው ልጅ አዕምሮ በመተንተን እንዴት እንደሚሰራ ለመረዳት ይሞክራል። ስለ ሰው ልጅ እውቀት፣ ስለ መንስኤና ውጤት፣ ስለ የሰው ልጅ ስሜትምና ስለ ደግና ክፉ ይፈላስፋል።
- An Enquiry Concerning Human Understanding (1748)
- በዚህች ትንሽ መጽሓፍ ውስጥ ከላይ የቀረበውን መጽሐፍ ሃሳቦች በማሳጠርና ለማንበብ እንዲመቹ በማድረግ ተንትኗል።
- An Enquiry Concerning the Principles of Morals (1751)
- ትንሽና ለማንበብ ምቹ የሆነች መጽሐፍ ስትሆን የመጽሐፉ ትኩረት ስለ ደግና ክፉ ይተነትናል
- Dialogues Concerning Natural Religion[1] (after Hume died)
- በዚህ መጽሐፉ 3 ገጸ ባህርያት ስለ አምላክ ሲከራከሩ ይነበባል