ዳዱሻ
ዳዱሻ በመስጴጦምያ የኤሽኑና ንጉሥ ነበረ (1712-1692 ዓክልበ. የነገሠ)። የ2 ኢፒቅ-አዳድ ልጅና የዳኑም-ታሃዝ ተከታይ ነበረ።
የዳዱሻ ዘመነ መንግሥት ከዓመት ስሞቹ መሃል ፱ ያህል ከሥነ ቅርስ ተገኝተዋል።[1] ቀደም-ተከተላቸው ግን አይታወቅም። ከነዚህ መካከል፦
- 1712 ዓክልበ. - «ዳዱሻ በአባቱ በት የገባበት ዓመት»
- b. - «ዳዱሻ የኤካላቱም ሠራዊት ያሸነፈበት ዓመት»
- g. - «ዳዱሻ ማንኪሱምን የያዘበት ዓመት።»
- 1692 ዓክልበ. - «ዳዱሻ ቃባሩምን የያዘበት ዓመት።»
በዚህ ዘመን ማንኪሱምና ኤካላቱም የ1 እሽመ-ዳጋን ግዛቶች ነበሩ፤ ይህም አባቱ 1 ሻምሺ-አዳድ የአሦር ንጉሥ እየሆነ ነው። የእሽመ-ዳጋን ደብዳበዎች ስለዚህ ዘመቻ ይታወቃሉ። በ1694 ዓክልበ. ዳዱሻ ከሻምሺ-አዳድ ጋራ በሰላም ተስማምቶ አብረው በአርቤላ ላይ ዘመቱ። «የዳዱሻ ጽላት» በመጨረሻው ዓመት ዳዱሻና ሻምሺ-አዳድ በአርቤላና ቃባሩም ንጉሥ ቡኑ-እሽታር ላይ ያደረጉትን ዘመቻ ይተርካል። የቡኑ-እሽታር ግዛት በሱባርቱ በዛብ ወንዝ ነበረ።
በአንዳንድ መምህር አስተሳሰብ ዳዱሻ የኤሽኑና ሕግጋት ያወጣቸው ንጉሥ ነው። ልጁም 2 ኢባልፒኤል ተከተለው።
ቀዳሚው ዳኑም-ታሃዝ |
የኤሽኑና ንጉሥ 1712-1692 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ 2 ኢባልፒኤል |