ዳሞት ፑላሳ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ውስጥ በወላይታ ዞን ሚገየኝ ወረዳ ነው። ዳሞት ፑላሳ ወረዳ በምስራቅ እና በደቡብ በዳሞት ጋሌ በምዕራብ በቦሎሶ ሶሬ እና በሰሜን ከሀዲያ ዞን ይዋሰናል። ዳሞት ፑላሳ በ1998 ዓ.ም ከዳሞት ጋሌ ወረዳ ተለይቷል። የወረዳው አስተዳደር ማዕከል ሻንቶ ከተማ ነው።

ዳሞት ፑላሳ
Damoota Pullaasa
ወረዳ
ሀገር ኢትዮጵያ
ክልል ደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት
ዞን ወላይታ ዞን
ርዕሰ ከተማ ሻንቶ

የስነ ሕዝብ አወቃቀር

ለማስተካከል

እ.ኤ.አ 2019 በማዕከላዊ እስታቲስቲክ ኤጀንሲ በተካሄደው የህዝብ ብዛት ትንበያ መሰረት [1] ይህ ወረዳ በድምሩ 135,760 ህዝብ ያለው ሲሆን ከነዚህም 66,463 ወንዶች እና 69,297 ሴቶች ናቸው። 5,346 ወይም 5.08% የሚሆነው የወረዳው ህዝብ የከተማ ነዋሪ ነው። አብዛኛው ነዋሪ ፕሮቴስታንቶች ሲሆን፣ 73.72% የሚሆነው ህዝብ ይይዛል፣ የሮማ ካቶሊክ እምነት ተከታዮች ደግሞ 17.1% ይይዛል፣ እና 8.17% የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች ናቸው።