ዲማምስራቅ ጎጃምእነማይ ወረዳ የሚገኝ ከተማ ነው። ይህ ቦታ በተለይ እውቅና እሚያገኘው የዲማ ጊዮርጊስን ቤተክርስቲያንና መናኞችና ሌሎች የሚጠለሉበት ገዳም በማቀፉ ነው።

ዲማ
ከፍታ 2,076 ሜትር
ዲማ is located in ኢትዮጵያ
{{{alt}}}
ዲማ

10°0′ ሰሜን ኬክሮስ እና 38°29′ ምሥራቅ ኬንትሮስ

በዓፄ ሱሰንዮስ ዘመን የነበሩትን ዓፄ ያዕቆብን ደግፈው ሲዋጉ በጎል ጦርነት ድል የሆኑት ራስ አትናቴዎስ በዲማ ገዳም እንደተጠለሉ በዚያው ዘመን የተጻፉ ድርሳናት ይገልጻሉ[1]። እንዲሁ ደጃዝማች ጎሹ ዘውዴ ልጃቸው ብሩ ጎሹ ሲያምጽ በዲማ ገዳም እንደተጠለሉ እንግሊዙ ሲ ቲ ቤኬ ዘግቦት ይገኛል።

በ19ኛው ክፍለ ዘመን፣ የዲማ ጊዮርጊስጎጃም ውስጥ ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ትልቁ ነበር[2]። ቤተ ክርስቲያኑ በ2 ሜትር ከፍታ የድንጋይ አጥር የታጠረ ሲሆን ውስጡ ብዙ ታሪካዊ መጻሕፍትን አካቶ ይዟል። በ1513 ዓ.ም. በአውሮጳውያን ስልት የተሳሉ የዓፄ ናዖድ እና ዓፄ ልብነ ድንግል ምስሎች በቤተርክስቲያኑ በሚገኙ መጽሐፍት ይታያሉ[3]

ማጣቀሻEdit

  1. ^ James Bruce, Travels to Discover the Source of the Nile (1805 edition), vol. 3, p. 280
  2. ^ http://www.nai.uu.se/library/resources/dossiers/local_history_of_ethiopia/d/ORTDIL05.pdf
  3. ^ http://www.nai.uu.se/library/resources/dossiers/local_history_of_ethiopia/d/ORTDIL05.pdf