ዮቃይድ ጎናት
ዮቃይድ ጎናት ከ252 እስከ 253 አም ድረስ የአየርላንድ ከፍተኛ ንጉሥ ነበር።
በአይርላንድ ታሪኮች ዘንድ ቀዳሚው ኮርማክ ማክ አይርት ከተገደለ በኋላ፣ ለአንድ አመት ከፍተኛ ንጉሥነቱን ያዘ፤ ከዚያ በውግያ ተገደለና የኮርማክ ልጅ ካይርብሬ ሊፌቃይር ከፍተኛ ንጉሥ ሆነ።
የቲገርናቅ ዜና መዋዕል (1080 ዓም ተቀነባብሮ) ዮቃይድን አይጠቅስም። ኮርማክ በ252 ዓም እንደ ሞተ ይዘግባል። የካይርብሬም ዘመን በ253 እንደ ጀመረ ሲለን በዚህ አቆጣጠር የዮቃይድ ዓመት 252-253 ዓም መሆን አለበት።