የዊሠ (ጥንታዊ እንግሊዝኛ፦ Gewisse) ከአንግሎ-ሳክሶን ሕዝቦች ሴያሕስ (ሳክሶን) ብሔር አንድ ነገድ ነበሩ። ከ677 ዓም በኋላ ስማቸው ወደ «ምዕራብ ሴያሕስ» (ወስት-ሴያሕስ ወይም ወሠክስ) መንግሥት ተቀየረ።

አንግሎ-ሳክሶን ዜና መዋዕል ዘንድ፣ «ዪዊስ» ከተባለ ቅድማያት ተሰየሙ። በጀርመንኛ «gewiss» /ገቪስ/ ማለት እስካሁን «እርግጥኛ» ሲሆን፣ «የዊሠ» ማለት ምናልባት «እርግጠኛ፣ ታማኝ» እንደ ሆነ ይታስባል። በሌላ አስተሳሰብ የ«የዊሠ» ስም ከጎረቤታቸው ነገድ «ኊቸ» ስም ጋር ተመሳሳይነት ስላለው ከዚያ ጋር መዛመዱ ይሆናል ይባላል።

በዜና መዋዕሉ ዘንድ መኮነናቸው ቸርድች መጀመርያ በ፭ መርከቦች በብሪታኒያ ጠረፍ ላይ በ487 ዓም ወረረ። ከ511 ዓም ጀምሮ ይህ ቸርድች የንጉሥነት ማዕረግ ወሰደ። በኋላ በንጉሣቸው ኪውነግልስ ሥር በ628 ዓም፣ የዊሠ ክርስትናን ተቀበሉ።

ከተከታዮቹ መሃል ማዕረጋቸው እስከ 677 ዓም «የየዊሠ ንጉሥ» ተባለ፣ ከንጉሥ ካድዋላ (677-681 ዓም) ጀምሮ ግን ይህ «የወስት-ሴያሕስ ንጉሥ» ሆነ።