የወፍ በሽታእንግሊዘኛው ደግሞ ጆንዲስ (jaundice) ራሱን የቻለ አንድ በሽታ ሳይሆን የብዙ በሽታወች ምልክት ነው። የወፍ በሽታ የሚከሰተው በደማችን የሚገኜው ቢሊሩቢን (bilirubin) የተባለው ኬሚካል መጠን ሲጨምር ነው። ይህ ከሚካልም ለቆዳችንና ለአይናችን ነጭ ክፍል ቢጫ ወይም ቢጫማ አረንጓዴ ቀለም ይሰጣቸዋል። ይህ ምልክት ብቻውን ወይም ከለሎች ምልክቶች ለምሳሌ ማሳከክ፤ የሰገራ ቀለም ወደ ቢጫነት እና የሽንት ወደ ጥቁርነት መቀየር እና ሆድ ህመም በተለይም በቀኝ በኩል ጉበት አካባቢ ይገኙበታል። የወፍ በሽታ በሁሉም እድሜ ክልል (ከጨቅላ ህጻናት እስከ አዋቂወች) ያሉ ሰወችን ያጠቃል። የወፍ በሽታ በጨቅላ ህጻናት ላይ ብዙውን ጊዚ በተወለዱ በመጀመሪያው ሳምንት የሚከሰት ሲሆን የከፋ ጉዳትም አያደርስም።

የወፍ በሽታ ከቀላል እስከ ከባድ በሆኑ በሽታወች ምክኒያት ሊመጣ ይችላል። በጤነኛ ሠው ደም ውስጥ ያለው የቢሊሩቢን መጠን ከ፩ ሚግ/ደሊ (1mg/dL) ያነሰ ሲሆን ይህ ምልክት ባለባቸው ሰወች ግን በትንሹ ከ ፪ ነጥብ ፭ እስከ ፫ ሚግ/ደሊ ነው። በተጨማሪም ይህ ምልክት ጨቅላ ህጻናት ላይ ሲከሰት የቢሊሩቢን መጠን ከ ፭ሚግ/ደሊ ያላነሰ መሆኑን ያመለክታል። ከፍተኛ የቢሊሩቢን መጠን ያልተጣበቀ (ኢ-ቀጥተኛ - unconjugated) ወይም የተጣበቀ (ቀጥተኛ - conjugated) ቢሊሩቢን ሊሆን ይችላል። ያልተጣበቀ ቢሊሩቢን መጠን መጨመር የቀይ ደም ህዋሳቶች መሞትን ሲያመለክት የተጣበቀ ቢሊሩቢን መጨመር ደግሞ የጉበት ወይም የሃሞት መፍሰሻ ቦይ ህመምን ያመለክታል። የወፍ በሽታ ህክምና እንደ አምጭው የበሽታ አይነት ይወሰናል። ይህም ከመድሃኒት እስከ ኦፕራሲዮን ድረስ ሊሆን ይችላል።

የወፍ በሽታ የሚያመጡ በሽታዎች

ለማስተካከል

ያልተጣበቀ የቢሊሩቢን መጠንን የሚጨምሩ በሽታወች

ለማስተካከል

እነዚህ በሽታወች በአጠቃላዩ የቀይ የደም ህዋሳትን ሞት በማስከተል ወይም የተመረተን ቢሊሩቢን ወደ ጉበት እንዳይገባ በማድረግ ያልተጣበቀ ቢሊሩቢን መጠንን የሚጨምሩ በሽታወች ናቸው። የቀይ የደም ህዋሳት ሞት ሂም (heme) የተባለ ንጥረ ነገር እንድመረት ያደርጋል። ይህ ንጥረ ነገርም ወደ ቢሊሩቢንነት በሰውነታችን የሚብላላ ይሆናል። ይህ ሁነታ በማንኛውም ሰው ላይ የሚካሄድ ቢሆንም በኢነዚህ በሽታወች ጊዜ ግን ከተለመደው መጥን ያለፈ ቢሉሩቢን እንዲመረት ያስከትላሉ። እነዚህ በሽታወችም በዘር ከሚተላለፉ እስከ ኢንፈክሽን ያሉ ናቸው።

የተጣበቀ ቢሉሩቢን መጠንን የሚጨምሩ በሽታወች

ለማስተካከል

ቢሊሩቢን በቀይ የደም ህዋሳት መሞት ምክኒያት ከተመረተ በኋላ ወደ ጉበት ይገባል። ጉበት ውስጥ ከገባ በኋላ ተብላልቶ ወደ ሃሞት ማፍሰሻ ቦይ፤ ከዛም ወደ ከጭን አንጀት የመጀመሪያው ክፍል ሁለተኛው ክፍል (the second part of duodenum) ይገባል። ከዛም ብዙው ወደ ጉበት የሚመለስ ሲሆን ( የተቀረው ደግሞ ከሰገራ ጋር የሚወጣ ይሆናል። ማንኛውም ይህን ሂደት የሚያስተጋጉል የጉበት ወይም ከዚያ በኋላ ያለ ችግር የተጣበከ ቢሊሩቢን መጠን መጨመርን ያመጣል።