የወታደሮች መዝሙር የሚባሉት አስራ ሁለት በጥንቱ አማርኛ የተጻፉ ግጥሞችን ነው። ከነዚህ ግጥሞች አራቱ በ1300ወቹ በአጼአምደ ጽዮን ዘመን የተጻፉ ሲሆን ምናልባትም በጣም ቀደመትና እስካሁን ካልጠፉ የአማርኛ ጽሁፎች መካከል ናቸው። [1]እኒህ አራቱ ግጥሞች በኤድዋርድ ኡልንድሮፍ የበለጠ ተጠንተዋል[2]። የመጀመሪያዎቹ ግጥሞች ስለ 15ኛው ክፍለ ዘመን ንጉስ፣ ስለ ቀዳማዊ አፄ ይስሐቅ የተገጠሙ ሲሆን ጣሊያናዊው ታሪክ ተማሪ ሴሩሊ የኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ ፈርጥ ካላቸው ወገን ናቸው። ቀሪዎቹ ግጥሞች ለዓፄ ዘርአ ያዕቆብና በኋላም ለዓፄ ገላውዲወስ የተገጠሙ ነበሩ።

የሚያዩት ገጽ ላይ ወይም እዚህ ላይ [1] በመጫን የመጽሐፉን ፲፬ ገጾች ማንበብ ይችላሉ

ከዚህ ጎን በ1881 በጣሊያን አገር ታትሞ ከወጣው የጥናት መጽሄት ሙሉው ፲፪ቱ ግጥሞች ቀርበዋል። የቃላቶቹ አጻጻፍ፣ አልፎ አልፎ አደናጋሪና በ1686ዓ..ም ለታተመው የአማርኛ መጽሐፍ መጽሐፈ፡ትምህርት፡ዘልሳን፡አምኅራ።‎ የቀረቡ ናቸው።

ከግጥሞቹ የተወሰደ

ለማስተካከል

እንዴት ታስደነግፅ

ደንጊያ በቁልቁለት ስሮጽ

እርሱ በእርሱ ሲፋለጽ

እንዴት ያስደነግጽ

እንዴት ታስደነግፅ

ኮከብ ትመስል ዣን በጽሩ ሰማይ ሲሮጽ

ወደ ምዕራብ ሲሠርፅ

ገጽኹ እንዴት ያስደነግፅ

ሲሬ ሠራዌ የመስል ዣን

ሐምበል አልብሶ ረመጽ

ጎድን በሪም ሲፈጸፍጽ

ሐንገት በሰይፍ ሲቆርጽ

ገጽኹ እንዴት ያስደነግፅ

ዣን ይስሐቄ ገጽ

ምላት የመስል ዣን

ሳፍ ለሳፍ ካንፈርዓጽ

ወርካ ከስሩ ነቅሎ ሲያሮጽ።

እንዴት ያስደነግፅ

ገጽኹ የዣን ይስሐቄ እንዴት ያስደነግጽ

ዣን ይስሐቄ ገጽ።

  1. ^ Huntingford,The Glorious Victories, pp. 129–134.
  2. ^ Edward Ullendorff, his review of Huntingford's translation of The Glorious Victories of Amda Ṣeyon, King of Ethiopia, Bulletin of the School of Oriental and African Studies, University of London, 29 (1966), p. 600