መጽሐፈ፡ትምህርት፡ዘልሳን፡አምኅራ።
መጽሐፈ፡ትምህርት፡ዘልሳን፡አምኅራ። በጀርመናዊው ጸሐፊ እዮብ ሉዶልፍ እና ኢትዮጵያዊው አባ ጎርጎርዮስ ትብብር የተደረሰ የአማርኛ ሰዋሰው ነበር። በላቲን ቋንቋ ግምገማ የተካሄደበት ይህ መጽሐፍ በ1686 ዓ.ም. ሊታተም በቅቷል።
መጽሐፉ፣ ከተለያዩ የሰዋሰው ጥናቶች በተጨማሪ የሉቃስ 11፡1-13 ትርጓሜን፣ አባ ጎርጎሪዮስ ስለ ቅድስት ማርያም የደረሱትን ምስጋና፣ ግጥሞችና የለተ ተለት ንግግሮችን መዝግቦ ይገኛል። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የሚገኙት አብዛኞቹ የአማርኛ ቃላት በርግጥም የአሁን ዘመን አማርኛን ለሚናገር ሰው እንግዳ አይደሉም። ሆኖም አልፎ አልፎ ለየት ያሉ የፊደላት አቀነባበር ይታያል። በአሁን ጊዜ «አ»ን የሚጠቀሙ ቃላት «ሐ»ን ሲጠቀሙ ይታያሉ፣ በአ እና ዐ ም መካከል ልዩ አጠቃቀም ይታያል። ሀ፣ ሐ እና ኅ እንዲሁ አገባብቸው ውሱንና የጠራ መሆኑ ግልጽ ነው።
በተረፈ አንድ አንድ ፊደላት ከአሁኑ ዘመን በተለይ መልኩ ሲቀረጹ ይታያሉ። ለምሳሌ ጨ ፊደል ጠ ሆኖ ከጎንና ጎኑ መያዣ ያለው ፊደል ሆኖ ቀርቧል። የመጽሐፉ ሙሉ ገጾች ከታች ቀርበዋል ፦