የካናዳ ጥንታዊ ኗሪዎችካናዳ አገር 1974 ዓ.ም. ሕገ መንግስት ሥር ኢንዲያን ("መጀመሪያ አገሮች" የተባሉ)፤ ሜቲ (ክልሶች)፤ እና እኑዊት (ወይም "ኤስኪሞ") ናቸው። እነዚህ 3 ክፍሎች አንድ ላይ ደግሞ "መጀመርያ ሕዝቦች" ይባላሉ። በካናዳ በተደረገው 1993 ቆጠራ ዘንድ፣ የጥንታዊ ኗሪዎች ብዛት ከ900,000 በለጠ። በዚህ ቁጥር ውስጥ 600,000 ከመጀመርያ አገሮች ዘር፤ 290,000 ሜቲ፣ እና 45,000 እኑዊት ይከተታሉ።

ባሕላዊ አለባበስ

የጥንታዊ ኗሪዎች ማህበራዊ ወኪሎች በካናዳ እንዲህ ናቸው፤ የመጀመርያ አገሮች ስብሰባ ለመጀመርያ አገሮች፤ እኑዊት ታፒሪት ካናታሚ ለእኑዊት፤ የሜቲ ብሔራዊ ጉባኤ ለሜቲ ናቸው።

ባለፈው ዐሥር አመት የካናዳ መንግሥት "የዘውድ ጉባኤ ስለ ጥንታዊ ኗሪዎች" (Royal Commission on Aboriginal Peoples) ሰበሰበ። ይህ ጉባኤ ያለፉትን መንግስት ዐቅዶች ስለ ጥንታዊ ኗሪዎች ለምሳሌ የሚሲዮን ተማሪ ቤቶች አመዛዝኖ ብዙ የአቅዋም ምክሮች ለካናዳ መንግስት አቀረበ።

ብዙ መጀመርያ አገሮች የሚኖሩት በተከለለ ቦታ ሲሆን፣ ብዙ ኗሪዎች ደግሞ ከቦታዎቹ ውጭ ይገኛሉ። የአገሮቹ ስሞች እንደሚከተለው ናቸው፦

 • ሚግማቅ ሕዝብ
 • ማለሲት ሕዝብ
 • አበናኪ ሕዝብ
 • አንሽናቤ (ኦጂብዌ) ሕዝብ
 • አቲካመክ ሕዝብ
 • ኔሂዮዋ (ክሪ) ሕዝብ
 • ወንዳት (ሁሮን) ሕዝብ
 • ሆደናሾኔ (ኢሮኰይ) ሕዝብ
 • ላኮታ (ሲው) ሕዝብ
 • ሲክሲካ (ብላክፉት) ሕዝብ
 • ሰይልሽ ሕዝቦች
 • ንስጋ ሕዝብ
 • ና-ዴኔ (አጣፓስካን) ሕዝቦች