የኩላሊት ጠጠር የሚያሳይ ባለ ቀለም ፎቶግራፍ

የኩላሊት ጠጠር የሚባለው በኩላሊት ውስጥ የጠጣር ነገሮች መጋገር ወይም መሰብሰብ ሲሆን የጠጣር ነገሮቹም ምንጭ በሽንት ውስጥ የሚገኙ የምግብ ንጥረ ነገሮች ናቸው::

የኩላሊት ጠጠሮች ብተለያየ መልኩ ይከፋፈላሉ፣ ከነዚህም ውስጥ; በሚገኙበት ቦታ [በሽንት ትቦ ወይም ዩሬተር, በሽንት ፊኛ]; በጠጠሮቹ ውስጥ በሚገኙ ማእድናት [ካልሺየም የያዙ, ስትራቫይት (ማግኒዢየም, አሞኒየም ፎስፌት), የሸንት አሲድ ወይም ሌላ ማእድናት]::

የኩላሊት ጠጠር የህመም ምንጭ ሲሆን በአብዛኛው ወንዶችን ያጠቃል (፹ በመቶ (80%)). ወንዶች በአብዛኛው የኩላሊት ጠጠር ህመም ከ ፴(30)-፵(40) ባለው እድሜአቸው ሲጀምራቸው ሴቶች ላይ ግን ዘግይቶ ይከሰታል::

የኩላሊት ጠጠሮች በአመዛኙ ምንም የህመም ስሜትና ጉዳት ሳያስከትሉ በሽንት መስመር ውስጥ አልፈው ከሰውነት ይወገዳሉ:: ነገር ግን ጠጠሮቹ በመጠን ከጨመሩ (፫(3) ሚሜ አካባቢ ከደረሱ) የሽንት ትቦ ሊዘጉ ይችላሉ:: የሽንት ትቦ በጠጠር መዘጋት ሽንት በቀላሉ እንዳይተላለፍ (ፓስቴርናል አዞቶሚያ) ብሎም ሽንት ወደ ሁዋላ በመመለስና በኩላሊት ውስጥ በመከማቸት ጉዳት ሊያደርስ ይችላል (ሃይድሮኔፕሮሊስ):: ይሄ ችግር (ሃይድሮኔፕሮሊስ) ከታችኛው የጎድን አጥንት አንስቶ እስከ የዳሌ አጥንት (ሂፕ) ድረስ ባለው ቦታ, በብሽሽትና በታችኛው የምግብ መፍጫ ክፍሎች (ሎወር አብዶሜን) አካባቢ ለህመም ስሜት (ሬናል ኮሊክ) ይዳርጋል::

ሬናል ኮሊክ ከማቅለሽለሽና የማስታወክ ስሜቶች, ትኩሳት , በሽንት ውስጥ ደም መኖር በሽንት ውስጥ መግል የሚመስል ፈሰሽ (ፐስ) እና በሽንት ጊዜ ከከፍተኛ የህመም ስሜት ጋር ሊያያዝ ይችላል:: የሬናል ኮሊክ የህመም ስሜቶች በአመዛኙ ከ ፳(20) እስከ ፷(60) ደቂቃ በሚሆኑ ተመላላሽ የህመም ስሜቶች የታጀበ ሆኖ ከታችኛው የጎድን አጥንት ወይም ከታችኛው የጀርባ ክፍል ተነስቶ ወደ ብሽሽት ወይም የሽንት መሽኛ ብልቶች የሚሰራጭ የህመም ስሜት ነው::

የኩላሊት ጠጠር መኖር በሰውነት አቁዋም ምርመራዎች (በበሽታ ምልክቶች መኖር (ፊዚካል ኤግዛሚኔሽን)), በሽንት ምርመራ, በራጅ ምርመራ እንዲሁም በበሽተኛው የበፊት የጤና ምርመራ ውጤቶች ድጋፍ ይታወቃል:: የአልትራሳውንድ እና የደም ምርመራዎችም የኩላሊት ጠጠር በሽታ መኖሩን ለማወቅ አጋዥ ይሆናሉ::

የኩላሊት ጠጠር ህመም ካላስከተለ የሰውነትን ሁኔታ እየገመገሙ በጥንቃቄ መጠበቅ ጥሩ አማራጭ ነው:: ህመም ለሚያስከትል የኩላሊት ጠጠር በሽታ የመጀመሪያ እርዳታ ህመሙን መቆጣጠር መሆን አለበት:: ይሄም በ ነን ስቴሮዳይዳል አንቲ ኢንፍላማቶሪ ወይም አፒኦዲስ መድሃኒቶችን በመጠቀም ነው:: ከፍተኛ የሆነ የኩላሊት ጉዳት ወይም ህመም ከተከሰተ ግን የቀዶ ጥገና አስፈላጊ ሊሆን ይችላል:: ለምሳሌ, አንዳንድ ጠጠሮች በነዛሪ ሞገድ (ሾክ ዌቨ) አማካኝነት ወደ ጥቃቅን ጠጠሮች መሰባበር ሲቻል በአንዳንድ ሁኔታ ደግሞ የሰውነት መቀደድን ሊያስከትሉ የሚችሉ ቀዶ ጥገናዎች አስፈላጊ ሊሆን ይችላል:: አንዳንድ ጊዜም በሽንት መሽኛ ትቦ ውስጥ ሌላ ሰው ሰራሽ ትቦ (ዩሬትራል ስቴንት) በመቀጠል በጠጠር የተዘጋውን ቦታ ወደ ጎን አልፎ እንዲሄድና የህመም ስሜቱን መቀነስ ይቻላል::

የበሽታ ምልክቶች

ለማስተካከል
 
የሬናል ኮሊክ የህመም ስሜት የሚከሰትበት የሠውነት ክፍል

የሽንት ትቦና የሽንት ትቦ ከኩላሊት ጋር የሚገናኝበት ቦታ (ሬናል ፔልቪስን) የሚዘጋ የኩላሊት ጠጠር ልዩ ምልክት ከታችኛው የጎድን አጥንት እስከ ብሽሽትና የሽንት ብልት ድረስ የሚደርስ ከፍተኛ የሆነ ተመላላሽ የህመም ስሜት ነው። ይሄ ሬናል ኮሊክ ተብሎ የሚታወቅ ልዩ የህመም ስሜት ሃይለኛ ተብለው ከሚታወቁ የህመም ስሜቶች የሚመደብ ነው።

በኩላሊት ጠጠር የሚከሰት ሬናል ኮሊክ ሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣትን፣ የድካም ስሜትን፣ በሽንት ውስጥ ደም መኖርን፥ ማላብን፣ ማቅለሽለሽና ማሥታወክን ሊያስከትል ይችላል። የህመም ሥሜቱም ተመላላሽ በሆነና ከ ፳(20)-፷(60) ደቂቃ ሲቆይ ህመሙም የሽንት ትቦ ጡንቻ ጠጠሮቹን ለማስውገድ በሚያደርገው የመኮማትርና የመፍታታት እንቅስቃሴዎች (ፐሪስታልቲክ) የሚከሠሰት ነው። በፅንስ መጠንሠስ ጊዜ በሚከሰት የሽንት መተላለፊያ፤ የሽንት መሽኛ ብልቶችና፤ የምግብ ትቦዎች (ጨጉዋራ፣አንጀት) የተፈጥሮ ግንኙነት ምክንያት የኩላሊት ጠጠር በሽንት ብልቶች ላይ ህመም ከማስከተሉም በላይ ለማቅለሽለሽና ለማስታወክም ይህ የተፈጥሮ ቁርኝት መንስኤ ነው። ፖስተርናል አዞቶሚያ እና ሃይድሮሄፕሮሊስ (ትርጉም ከላይ) በአንዱ ወይም በሁለቱ የሽንት ትቦዎች መዘጋት ምክንያት ይከሠታል።

መንስኤዎች

ለማስተካከል

ለኩላሊት ጠጠር መፈጠር ምክንያት ሊሆኑ ከሚችሉ የአመጋገብ ልምዶች መካከል፤ ውሃ በበቂ አለመጠጣት፣ ከፍተኛ የሆነ የእንሥሳት ሥጋ (ፕሮቲን) መመገብ፣ ጨው (ሶዲየም)፣ የተጣሩ ስኳሮች፣ የፍራፍሬ ስኳር (ፍሩክቶስ)፣ ኦክሳሌት (C2O42−) የያዙ ምግቦች (ኦክሳሌት በብዙ ዕፅዋት ውሥጥ የሚገኝ ንጥረ ነገር ሲሆን በተለይም በሰባ ዶሮ፣ በጥቀር አዝሙድ??? (ብላክ ፒፐር)፣ ፐርስሊ፣ ስፒናች፣ ካካዎ፣ ቸኮላት፣ ኦቾሎኒ፣ አብዛኛዎቹ እንጆሬዎች ውስጥ ይገኛል)፣ የአፕል ጭማቂ እና የኮላ መጠጦች ናቸው።

የመከላከያ መንገዶች

ለማስተካከል

የኩላሊት ጠጠርን ለመከላከል የሚደረጉ ጥረቶች በታማሚው ውስጥ በሚገኘው የኩላሊት ጠጠር አይነት (የማዕድን ይዘት) ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት። የአመጋገብ ሥልት በኩላሊት ጠጠር መፈጠር (መከማቸት) ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሊያደርግ ይችላል። የኩላሊት ጠጠርን መፈጠርን መከላከል (መቀነስ) የሚቻለው የአመጋገብ ሥልትን በማስተካከልና በሽንት ውስጥ የሚገኙ ለኩላሊት ጠጠር መከማቸት መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ የማእድናትን መጠን ለመቀነስ የሚረዱ መድሃኒቶችን በመጠቀም ነው። የህክምና ባለሙያዎች የሚከተሉትን የአመጋገብ ሥልቶችን መከተል የኩላሊት ጠጠርን ለመቀነስ እንደሚረዳ ያመለክታሉ፤

  • ሲትሬት (በሎሚና በብርቱካን ውስጥ የሚገኝ አሲድ ነው) ያላቸውን ፈሳሾች በብዛት መጠጣት፣ የፈሳሽ አወሣሠዱም በብዛትና በቀን እስከ ሁለት ሊትር የሽንት መጠን እሰኪደርስ ቢሆን ይመከራል። በዚህ መንገድ የሽንትን ፒኤች 6.5 አካባቢ በማድረግ በተለይ በሽንት አሲድ (ዩሪክ አሲድ) ምክንያት የሚመጡ ጠጠሮችን ለማስወገድ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያደርጋል።
  • የካልሺየም አወሳሰድ መጠንን ከ 1000-1200 ሚግ መጠን በቀን ውስጥ ከፍ ማድረግ
  • የሶዲየም አወሳሰድ መጠንን ከ 2300 ሚግ በቀን በታች እንዲሆን ማድረግ
  • የቪታሚን ሲ የቀን ፍጆታን ከ 1000 ሚግ በቀን በታች እንዲሆን ማድረግ
  • የእንሥሣት ፕሮቲን (ስጋና ሥብን) ከሁለት ጊዜ በታች ማድረግና መጠኑንም ከ 170-230 ግራም እንዳያልፍ መቆጣጠር እና
  • ኦክሳሌት የያዙ ምግቦችን (ከላይ ተጠቅሰዋል) መቀነስ ናቸው።