ኩላሊት
ኩላሊት በሰዎችና በብዙ እንስሶች ውስጥ ሽንት የሚሠሩት አካላት ናቸው።
የቃሉ «ኩላሊት» መነሻ ከግዕዝ «ኲሊት» እና በተለይ ከዚሁ ግዕዝ ቃል ብዙ ቁጥር («ኲሊያት») ነበር።
ከ4 መቶ ዓመታት በፊት፣ ኩላሊት የኅሊና መቀመጫ መሆኑ በአውሮፓ በሰፊ ይታመን ነበር። ይህም የተነሣ ከዕብራይስጥ መጽሐፍ ቅዱስ (መዝሙር 7:9) እንዲሁም በከአዲስ ኪዳን (የዮሐንስ ራዕይ 2:23) መሠረት ነው። የዛሬ ሕክምና ሊቃውንት ግን ኩላሊት እንዲህ አይነት ሥነ ልቡናዊ ሚና እንዳለው አይቆጠሩም። የሚያስደንቀው ግን አድሬናል ሆርሞን (ኩላዕጢ እድገንጥር) ወይም ግላንድ (ኩላትጌ ዕጢ) የሚገኘው በኩላሊት በላይኛው ክፍል ነው!!! ታላቅ ደስታ ወይም ድንጋጤ ሲገጥመን ሰውነታችንን መቆጣጠር እስኪያቅተው ድረስ ለዐይምሮዋችን መልክት የሚያስተላልፍ ክፍል ነው ። ብቻ ከፍተኛ ግንኙንት ከዐይምሮዋችን ጋር አለው ፤ ለምሳሌ የፋይት ኦር ፍላይት ስሜታችንን ይቆጣጠራል።