የኢትዮጵያ ካርታ 1459 በዝርዝር
ይህ ካርታ የቬኒስ፣ ጣሊያን መነክሴ የነበረው ፍራ ማውሮ በ1459 አዘጋጅቶት ከነበረው የፍራ ማውሮ ዓለም ካርታ የተወሰደ ነው። ካርታው ደቡብን ወደላይ ሰሜንን ወደታች ዘቅዝቆ ስለሆነ የሳለው ለመረዳት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። ሞቃዲሾንና የሶማሊያን ጠረፍ በመመልከት የአፍሪቃ ቀንድን በውል ማስተዋል ችላል። ካርታው ላይ diab የተሰኘው ሶማሊያ ሊሆን እንዲችል ሞቃዲሾን ማስተዋል ይረዳል። ከዚህ አነስ ብሎ የቀረበውን የፍራማውሮ ካርታ (ከጥቂት የእንግሊዝኛ ትርጉሙ ጋር ለማየት) እዚህ ቀርቧል፡ የኢትዮጵያ ካርታ 1459
ስለካርታው ትችትና ቁምነገር፡-
- ካርታው ላይ Xegiba የሚለው አረቦች ለZanzibar የሚጠቀሙበት ስምን ነበር። Chelue እንዲሁ ለKilwa እና Maabase ለMombasa (ሞምባሳ፣ ኬኒያ) ነው።
- ካርታው ላይ Mareb እና Tagas ወንዞች መረብ እና ተከዜ ወንዞችን የሚያመላክቱ ናቸው። Mana, Lare እና Abavi በእንግሊዝኛው Mareb(መረብ), Takkazye(ተከዜ), Menna(መና), Tellare(አጥባራ) እና Abbai (አባይ) ናቸው። * Xebi and Avasi የሚሉት የደቡብ ኢትዮጵያን ወንዞች ግቤ እና አዋሽ ወንዝን ያመላክታሉ።
- Zebe የሚያመላክተው Webi Shebeli (ዋቢ ሸበሌ) ነው።
- ናይል (አባይ) ከጣና ሃይቅ ይነሳል። ይህ አካባቢ Fountain of Genet (የገነት ፏፏቴ) ይለዋል። በዚህ ስም ይህ አክባቢ እስከ 18ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ይታወቅ ነበር።
በዚህ በጥንት ዘመን እኒህን በጣም ትክክል መረጃወችን የያዘው የጣሊያኑ ካርታ ይህን መረጃ ያገኘው ወደ ጣሊያኑ ፍሎረንስ ከተላከው የኢትዮጵያ ሚሲዮን (1441) እንደሆነ ግምት አለ።
- ካርታው ላይ እንደሰፈረው በ1430 የኢትዮጵያው ንጉስ (ቀዳማዊ አምደ ጽዮን ) የdiabን እጅግ ለም የሆነ አገር እንደተቆጣጠረ ይናገራል። ተመራማሪወች ይህ ቦታ የሶማሊያ ባህረ ሰላጤን ያመላክታል ይላሉ።
- ከጣና ሃይቅ አጠገብ የምናየው Ciebel gamar ሲተረጎም mountain of the moon ማለት ነው። የናይል ወንዝ መነሻ መሆኑ ነው። ለምድር ወገብ የተሰጠው ስያሜ Equator የመጣው ከዚህ ተራራ ስም ነው።
- ፍራ ማዉሮ ሲጽፍ << የአገሩ ሰወች በራሳቸው እጅ ከተማቸውን፣ ወንዛቸውንና ተራሮቻቸውን ከነስማቸው እንዲስሉልኝ አደረኩ። ነገር ግን ከብዛታቸው የተነሳ ሁሉንም ልመዘግብ አልቻልኩም ምክንያቱም ቦታ አይበቃም>> ።
የፍራ ማሮ ካርታዎች በዝርዝር | ||
---|---|---|