ከመጀመሪያው የኢትዮጵያ ካርታ በስተቀር በታሪክ የምናገኛቸው ካርታወች ኢትዮጵያን በውል የማያውቁ ግን በስራው የተካኑ አውሮጳውያን የሰሩዋቸው ናቸው። ካርታቸውንም ያቀናብሩት የነበር ከአይን እማኞችና ተጓዦች ጽሁፍ ነው። ስለዚህም ስህተት መፈጠሩ አይቀሬ ነበር። ሆኖም ግን በታሪክ አጋጣሚ የኢትዮጵያውን ሚሶዮን ወደ ፍሎረንስ ከተማ (1441) የመጀመሪያውን የኢትዮጵያ ካርታ በራሳቸው እጅ ስለው ለካርታ ሰሪው ፍራ ማውሮ በማቅረባቸው በታሪክ የምናገኘው ቀደምቱ በፍራ ማውሮ የተሰራው የኢትዮጵያ ካርታ (1459) ከሞላ ጎደል ትክክል ሆኖ እናገኘዋለን። ዝርዝር ቦታወቹም በአብዛኛው ከአሁኑ ዘመን ቦታወች ጋር የሚገጥሙ ናቸው። ፍራ ማውሮ እንደጻፈው በርግጥም በካርታው ላይ ከቀረበው በላይ መረጃ በኢትዮጵያኑ ሚስዮን ቀርቦለት ነበር ሆኖም ግን በቦታ መጣበብ ምክንያት ሳይመዘግብው ቀርቷል። ሁለተኛው፣ በዝርዝሩና ትክክለኛነቱ ቀደምት የሆነው ካርታ የ1690ው የኮርኔሊ ቬንቼንዚ ነው። ይህ ካርታ በፖርቱጋል ተጓዦች እማኝነት መሰረት የተሰራ ነው። ካርታው ከሱ በፊትም ሆነ በኋላ ከተሰሩት በዝርዝር አቀማመጡና በ ትክክለኝነቱ የበለጠ ሆኖ እናገኘዋለን።


ሙሉው የኢትዮጵያ ካርታወች ዝርዝር በየዘመናቱ እትች መደቡ ላይ ተለጥፏል። ተጭነው ያንብቡ።