የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ 961

በረራ ቁጥር 961 ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ ቦይንግ 767-260ER አውሮፕላን ኅዳር ፲፬ ቀን ፲፱፻፹፱ ዓመተ ምሕረት ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ሲሄድ ተጠልፎ ነበር። አገልግሎቱ ከቦምቤይ-አዲስ አበባ-ናይሮቢ-ብራዛቪል-ሌጎስ-አቢጃን ነበር። ይህ የአውሮፕላን ጠለፋ የተደረገው አውስትራልያ የፖለቲካ ጥገኝነት በሚፈልጉ ሦስት ኢትዮጵያውያን ነበር።

የአደጋው ምስል
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ 961 የመቀመጫዎች ንድፍ

አውሮፕላኑ የህንድ ውቅያኖስ ላይ ሲሸልስ ደሴት አካባቢ ሲደርስ በነዳጅ እጥረት ምክንያት ተከሰከሰ። በዚህም ጠላፊዎቹን ጨምሮ ከ175 ተሳፋሪ መንገደኞች እና የአውሮፕላን ሰራተኞች ውስጥ 125 ለሞት ተዳርገዋል። 50 የሚሆኑት ከጉዳት ጋር ለመትረፍ ችለዋል። ይህ አደጋ በደረሰበት ጊዜ አደጋው ከፍተኛ አሰቃቂ አደጋ በመሆን 2ኛ ሁኖ ተመዝግቧል[1]

ይዩ ለማስተካከል

ማጣቀሻ ለማስተካከል

  1. ^ "Corrections." The New York Times. November 27, 1996. Retrieved on August 19, 2014.

ድር ጣቢያ ለማስተካከል

 
በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለ Ethiopian Airlines Flight 961 የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።