የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር
በዘመነ ኢህአዴግ
ለማስተካከልየዜግነት ክብር በኢትዮጵያችን ፀንቶ ታየ ህዝባዊነት ዳር እስከዳር በርቶ ለሰላም ለፍትህ ለህዝቦች ነፃነት በእኩልነት በፍቅር ቆመናል ባንድነት መሰረተ ፅኑ ሰብዕናን ያልሻርን ህዝቦች ነን ለስራ በስራ የኖርን ድንቅ የባህል መድረክ ያኩሪ ቅርስ ባለቤት የተፈጥሮ ፀጋ የጀግና ህዝብ እናት እንጠብቅሻለን አለብን አደራ ኢትዮጵያችን ኑሪ እኛም ባንቺ እንኩራ።
- ግጥም፦-ደረጀ መላኩ መንገሻ፤
- ዜማ፦- ሰሎሞን ሉሉ ምትኩ
በዘመነ ደርግ
ለማስተካከልኢትዮጵያ ኢትዮጵያ -ኢትዮጵያ ቅደሚ በኅብረተሰባዊነት - አብቢ ለምልሚ! ቃል ኪዳን ገብተዋል - ጀግኖች ልጆችሽ ወንዞች ተራሮችሽ - ድንግል መሬትሽ ለኢትዮጵያ አንድነት - ለነፃነትሽ መስዋዕት ሊሆኑ - ለክብር ለዝናሽ! ተራመጂ ወደፊት - በጥበብ ጎዳና ታጠቂ ለሥራ - ላገር ብልጽግና! የጀግኖች እናት ነሽ - በልጆችሽ ኩሪ ጠላቶችሽ ይጥፉ - ለዘላለም ኑሪ።
- ግጥም፦-በአሰፋ ገብረማርያም
- ዜማ፦-አቶ ዳንኤል ዮሐንስ
በንጉሱ ዘመን
ለማስተካከል(ማርሽ ተፈሪ)
ኢትዮጵያ ሆይ ደስ ይበልሽ በአምላክሽ ኃይል በንጉስሽ ተባብረዋልና አርበኞችሽ አይነካም ከቶ ነፃነትሽ ብርቱ ናቸውና ተራሮችሽ አትፈሪም ከጠላቶችሽ። ድል አድራጊው ንጉሣችን ይኑርልን ለክብራችን።
በ1919 ዓ.ም፤ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት (አጼ ቀደማዊ ኃይለ ሥላሴ)
- ግጥም፦-በቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ
- ዜማ፦-ኬቮርክ ናልባንዲያን፦ ደረጃ በጋሻዉ